በሀገሪቱ በሚገነቡ የጤና ተቋማት ላይ የሚታየው የዲዛይን ችግር በአፋጣኝ ተፈቶ ወደ ስራ እንዲገቡ የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ

ባህር ዳር፡ ግንቦት 12/2009 ዓ/ም(አብመድ)በሃገሪቱ የሚከናወኑ የጤና ተቋማት ያለባቸውን የዲዛይን ግንባታ ችግር እዲፈቱ ለማድረግ የሚያስችል ጉብኝት በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተከናውኗል፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃነ የጤና ተቋማት ሲገነቡ የሚታይባቸውን ችግር አስተካክለው አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ግንባታ በሚከናወንባቸው አካባቢዎች ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በሰጡት አስተያየት እንዳሉት የሆስፒታል፣ የጤና ጣቢያ ፣የደም ባንክና መሰል ግንባታዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆኑን አውስተው እነዚህ ግንባታዎች ያሉበትን ደረጃ ከማየት ባለፈ የኔ የጉብኝት አላማ በእነዚህ ተቋማት ላይ የሚታየውን የዲዛይን ችግር በመመልከት ማስተካከያ ተደርጎባቸው ወደስራ እንዲገቡ ለማስቻል የሚለው የመጀመሪያ አላማችን ሲሆን ፤ሁለተናው አላማ ነባር ሆስፒታሎች ከድንገተኛ ህክምና ጋር በተገናኘ ያለባቸውን ችግሮች በማየት ተጨማሪ ግብዓት ከፌደራል የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት ነው ብለዋል፡፡

ፕሮፌስር ይፍሩ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል በሃገሪቱ ልዩ የህክምና አይነቶችን ለመስጠት እያደረገ ያለው ጥረት ተመልክተናል ፡፡ በሆስፒታሉ ብዙ ግንባታዎች እየተገነቡ ተመልክቻለው ይህ ሆስፒታል የዚህ ዞን ብቻ ከመሆን ያለፈ ሪፈራል ሆስፒታል ሆኖ በሃገሪቱ አንዳንድ ለየት ያሉ ህክምናዎችን በመስጠት እያደረገ ያለው ጥረት ሰፊ እንደሆነ ተረድተናል፡፡በመሆኑም በፌደራል ጤና ጥበቃ ደረጃ ብዙ ምናግዘው ይኖራል ብለዋል፡፡

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ጉብኝታችን መስተካከል ያለባቸውን ጉዳዮች ተመልክተናል የሚሉት ሚኒስትሩ ፕሮፌስር ይፍሩ በዋናው የጎንደር ሆስፒታል ግንባታ ላይ አዲስ ለማስፋፋት እየተሰራ ባለው እና አዘዞ ላይ እየተሰራ ባለው ግንባታ ላይ ብዙ የሚጎሉ ነገሮችን ተመልክተናል እንዲስተካከሉም መተማመን ላይ ደርሰናል ብለዋል፡፡

እንደ ሚኒስትሩ ፕሮፌስር ይፍሩ ገለጻ ዩኒቨርሲቲው እያሰራው ያለው ሆስፒታል እጅግ ዘመናዊ የሚበላል ነው ግን ደግሞ በምልከታየ ብዙ የሚስተካከሉ ነገሮች አሉት ይህን አስተካክለው ወደ ስራ እንዲገባ በእኛ በኩል የተለያዩ ድጋፎችን እንሰጣለን፡፡
ከዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች የምንጠብቀው አገልግሎት መስጠት ብቻ ሳይሆን በትምህርቱ ዘርፍ በተለይ በድህረ ምረቃ ትምህርት ስፔሻላዜሽን ትኩረት የምንሰጠው ስለሆነ ከጎንደር በተጨማሪ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በስፋት እንዲሰጥ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በኩል እገዛ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ 
በክልሉ ባሉ ነባር እና አዲስ የጤና ተቋማት ያለባቸውን የላብራቶሪ እና የግብአት አቅርቦት ችግር ለመፍታት አሰራሮችን የመወቀየር ስራ ሚኒስቴር መስራቤቱ እንደሚሰራ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጧል፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3161819
  • Unique Visitors: 186711
  • Published Nodes: 2579
  • Since: 03/23/2016 - 08:03