ቀይ ሽንኩርትን በጥሬው ከትፎ መመገብ ያለውን የጤና ጥቅም በጥቂቱ እነሆ፤-

ባሕር ዳር ፡የካቲት 16/2008 ዓ/ም(አብመድ)

-ቀይ ሽንኩርት ፋይበር፤ ፖታሺየም ፤ቫይታሚንእና ቫይታሚንበውስጡ የያዘ የአትክልት ዘር ነው፡፡

-ቀይ ሽንኩርት በጥሬው ከትፎ መመገብ ጉንፋን፤ ሳል፤ ትኩሳት እና ሌሎች አለርጂክ ነክ በሽታዎችን ለመከላከል ያግዛል፡፡

በተጨማሪም፤- የቀይ ሽንኩርት ጭማቂን በማር መጠጣትም ከላይ የተጠቀሱትን በሽታዎች በፍጥነት ለመከላከል ያስችላል፡፡

-ሰውነታችንን ትኩሳት ሲኖረው አንዲት የቀይ ሽንኩርት ቁራጭ በግንባራችን ላይ መያዝ ቶሎ እንዲሻለን ያደርጋል

-ተደጋጋሚ ነስር የሚያስቸግረን ከሆነም እንዲሁ የቀይ ሽንኩርት ቁራጭ በአፍንጫ ቀዳዳ ስር መያዝ መፍትሄ ነው

- በእንቅልፍ እጦት የሚሰቃዩ ከሆነም ቀይ ሽንኩርትን በጥሬው ከትፎ ከተመገቡ ጥሩ እንቅልፍ ይተኛሉ

-በተደጋጋሚ የምግብ መፈጨት ችግር ካጋጠመዎትም ቀይ ሽንኩርትን በጥሬው ከትፎ በመመገብ የምግብ መፈጨት ሂደቱ ተስተካከለ እንዲሆን ማድረግ ይቻላል፡፡

ታዲያ ቀይ ሽንኩርትን በጥሬው ከትፎ መመገብ ይህን ያህል ጠቀሜታ ካለው ዘወትር ምግብ ስንሰራ ሽንኩርቱን ድቅቅ አድርገን ከትፈን ብስል እና ክሽን አድርገን መመገባችን ቀይ ሽንኩርት ለጤና ሊሰጥ የሚገባውን ጥቅም እንዳይሰጥ አድረገናል አያስብል፡፡

ጤና ይስጠን

በአማራ ቴሌቪዥን ፣በአማራ ራዲዮ እና በኤፍኤም ባህር ዳር 96.9 ዜናዎች እና ዝግጅቶች ዙሪያ ለሚኖርዎት ጥቆማና አስተያየት ለአማራ ቴሌቪዥን(ATVን)፣ ለአማራ ራዲዮ(ARን) እና ለኤፍኤም ባህር ዳር 96.9 (FMን) በማስቀደም በ8200 ማድረስ ይችላሉ፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3537554
  • Unique Visitors: 199679
  • Published Nodes: 2652
  • Since: 03/23/2016 - 08:03