መንግስት ለብዝሃ ህይወት መጠበቅ ትልቁን ድርሻ የሚወስዱትን ቤተክርስትያናትን የጋራ ሀብት ናቸው ብሎ መንከባከብ አለበት-ዶክተር አለማየሁ ዋሴ

ባህር ዳር፡ ግንቦት 16/2009 ዓ/ም(አብመድ)የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአካባቢና ብዝሃ ህይወት ጥበቃ እያበረከተች ያለው አስተዋፅኦ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አንድ ጥናት አመላከተ፡፡

በባህር ዳር ከተማ ቤተክርስትያኗ ለብዝሃ ህይወት ጥበቃ የሚኖራት አስተዋጾና የሚያጋጥሙ ችግሮች የሚል አውደ ጥናት ተካሂዷል፡፡

የብዝሃ ህይወት ባለሙያና ጥናቱን ያቀረቡት ዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ እንዳሉት ‹‹የሀገራን የሴሜኑ የተፈጥሮ ደን ወድሟል ወደ ሚባልበት ደረጃ ደርሷል፡፡ይሁንና የቤተክርስትያንና የገዳማት ደኖች ለዘመናት ተጠብቀው የጥንቱን ደን ቅሪት በዝርያና በብዝሃ ህይወት አይን ስናየው እንዳይጠፉ ጠብቃ ይዛለች፡፡አካባቢው እንዲያገግም የዘር ምንጭ በመሆን እያገለገሉ ነው››፡፡

 

ይሁንና ለአዳዲስ ቤተክርስትያኖች ማስፋፊያ በሚል እየተቆረጡ ነው ፡፡ትኩረት ይሻሉ  ሲሉ ተሳታፊዎች  ተናግረዋል፡፡ህ ወጥቶለትም ቤተክርስትያኗ ተጠቃሚ የምትሆንበት መንገድ በፖሊሲ ደራጃ መፍትሄ መዘጋጀት አለበትም ብለዋል፡፡

ቤተክርስትያኗ ብዝሃ ህይወት አያያዟን እንደቀደመው ተግባሯ በመፈጸም መንግስትም ደግሞ አብሮ ሊሰራ ይገባል፡፡ምዕመናኑም ሀብቱ ወደ ሌላ አካባቢ እንዲስፋፋ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት አለባቸው ፡፡መንግስትም የጋራ ሀብት ናቸው ብሎ መንከባከብ አለበት ሲሉ አሳስበዋል ጥናት አቅራቢው ዶክተር አለማየሁ ዋሴ ፡፡

 

 

          በቤተ ክርስቲያኗ ዙሪያ ያሉ እፅዋት ተጠብቀው እንዲዘልቁ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እንዲሰሩም ጥናቱ አስገንዝቧል፡፡

አብዮት ከፋለ

 

ተጻፈ በመሰረት አስማረ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3537575
  • Unique Visitors: 199679
  • Published Nodes: 2652
  • Since: 03/23/2016 - 08:03