ሎጎ ሀይቅ አደጋ ላይ ነው፡-ኑሯቸው በሀይቁ ላይ የተመሰረተ ነዋሪዎች

ባህር ዳር፡ ግንቦት 18/2009 ዓ/ም(አብመድ)ለረዥም ጊዚያት በሎጎ ሀይቅ ላይ ህይወታቸውን መስርተው ኣሳ በማስገር የሚተዳደሩት አቶ ሰለሞን ተክሉ ሀይቁ እየሸሸ የአሳ ዝርያዎች እየተመናመኑ ነው ፡፡ ሀይቁ ከጊዜ ወደ ጊዜ ህልውናው አደጋ ላይ ነው፡፡የምናውቀው ማዕበል እንኳን የለም ሀይቁ በደለል በመሞላቱ  ብለዋል፡፡

በሀይቁ ዙሪያ ከሚገኘው  ሀይቅ እስጢፋኖስ ገዳም   ለ22 አመታት የኖሩት  አባ ተስፉ ስላሴ ወልደ ሀና ሀይቁ የነበረበትን ቦታዎች ምልክት አስቀምጨ የተቀመጡትን ምልክቶች ስለካቸው 38 ሜትር ሸሽቷል፡፡የአሳው ምርትም ቀንሷል ብለዋል፡፡

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ሀይቁን ለመታደግ ጥናት በማድረግ አውደ ጥናት አካሂዷል፡፡በምርምሩ መሰረትም በምጥፋት ላይ ያለውን ቀረሶ የተባለውን የአሳ ዝርያ ወደ ሀይቁ በማስገባት እንደገና እንዲስፋፉ እያደረገ ነው ያሉት አቶ አደም ሙሀመድ ናቸው፡፡

ዩኒቨርሲቲው ምርምር በማድረጉም 80 የአሳ ጫጩቶችን በማራባት 18 ሺህ ማድረስ ችሏል  ይላሉ አባ ተስፉ ስላሴ ወልደ ሀና፡፡

ወሎ ዩኒቨርሰቲ የአካባቢውን ማህበረሰብ በማሰልጠንም ሀይቁን ለእርሻ ከሚጠቀሙበት ይልቅ ለአሳ ምርት እንዲጠቀሙበት እያደረገ ነው፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን የሚገኘው  ሎጎ ሀይቅ  ከዚህ በላይ ጥናት ተደርጎ ህልውናውን መታደግ ካልተቻለ አሁንም አደጋ ላይ ነው፡፡

ጀማል ሙሀመድ

ተጻፈ በመሠረት አስማረ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3161855
  • Unique Visitors: 186711
  • Published Nodes: 2579
  • Since: 03/23/2016 - 08:03
 
Error | AMMA

Error

The website encountered an unexpected error. Please try again later.