ሊባኖስ በስለላ የጠረጠረችውን የእስራኤል አሞራ አገተች

ባሕር ዳር፡ ጥር 24 /2008 ዓ.ም (አብመድ)

ሊባኖስ ከእስራኤል ግዛት ተነስቶ ወደሃገሯ የገባውን አሞራ በሰላይነት በመጠርጠር በቁጥጥር ስር ማዋሏን የሃገሪቱን ብዙሃን መገናኛ ጠቅሶ ሲኤን ኤን ዘግቧል፡፡

ጋምላ የተባለው የእስራኤል የአራዊት መጠበቂያ ፓርክ እንዳስታወቀው አሞራው ከእስራኤል ጥቂት ኪሎሜትሮች ርቆ በደቡብ ሊባኖስ መንደር ነዋሪዎች መያዙን አስታውቋል ፡፡

ለመንደሯ ሰዎች ጥርጣሬ መነሻ የሆነው አሞራው የእስራኤል ፊደል የተቀረጸበት ቀለበት እና የአድራሻ ማሳወቂያ ሚጢጢ መሳሪያ ታስረውበት መገኘቱ ነው፡፡

የእስራኤል ቴል አቪቭ ዩኒቨርሲቲ አርማ ያለበት ቀለበት እግሩ ላይ የታሰረበትና ክንፎቹ ስር የአቅጣጫ መጠቆሚያ መሳሪያ የተጣበቀበት አሞራ መገኘቱን ተከትሎ በርካታ ምስሎች በተለያዩ ሚዲያዎች ተለቀዋል፡፡

የቴል አቪቭ ዩኒቨርሲቲ የወፍ ዝርያ አጥኚ የሆነው ኦሃድ ሃትዞፍ በጎላን ኮረብታዎች ላይ የሚገኘው የአሞራ መጠበቂያ ዋና አላማ እየጠፉ ያሉ የአሞራ ዝርያዎችን በመንከባከብ እንዲራቡ ማድረግ ነው ብሏል፡፡

አሁን በተያዘው አሞራ ላይ ያለው ምልክትና አቅጣጫ መጠቆሚያ ደህንነቱን ለመከታተል የተደረገ እንጂ ተጠራጣሪ ወገኖች እንደሚያስቡት ለስለላ ተግባር የተሰማራ አይደለም በማለት ባለሙያው አስረድቷል፡፡

የእስራኤል የስለላ ድርጅት ሞሳድ የቱሪዝም ኢንዱስትሪየን አደጋ ላይ ለመጣል በቀይ ባህር መዝናኛ ዳርቻዎች የሻርክ መንጋ አሰማርታብኛለች በማለት ግብጽ እ.ኤ.አ. በ2010 ያቀረበችውን አቤቱታ እስራኤል ውድቅ ማድረጓ ከዚህ ቀደም ተዘግቧል፡፡

ምንጭ፡- CNN

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3161884
  • Unique Visitors: 186711
  • Published Nodes: 2579
  • Since: 03/23/2016 - 08:03