ለ17 ኣመታት የጓጉለትን ያህል በ6 ህጻናት ተካሱ

ባህር ዳር፡ ግንቦት 20/2009 ዓ/ም(አብመድ)አዴቦዬ እና አጂቦላ ታይዎ ትዳር መስርተው ለ17 ዓመታት ልጅ ለማግኘት ቢመኙም ሳይሳካላቸው ቆይቶ ሰሞኑን በአንድ ጊዜ የ3 ሴትና የ3 ወንዶች ወላጆች መሆናቸውን ሲኤንኤን ዘግቧል ፡፡

በአሜሪካ- ሪችሞንድ ቨርጂኒያ ኮመንዌልዝ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ማዕከል ከ30 ሳምንታት እርግዝና በኋላ በቀዶ ህክምና የተገላገለችው ናይጄሪያዊቷ አጂቦላ ታይዎ እና ባለቤቷ ልጅ ወልዶ ለመሳም ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖራቸውም ባለመሳካቱ ተስፋ ወደመቁረጥ ተቃርበው እንደነበር ተናግረዋል ፡፡

አጂቦላ የስድስት ልጆች እናት እንደምትሆን በሃኪም ከተነገራት ቀን ጀምሮ 40 የጤና ባለሙያዎች የያዘ ቡድን ክትትል ከማድረግ  ባለፈ እንዴት ማዋለድ እንደሚቻል ቡድኑ ልምምድ ሲያደርግ በመቆየቱ ለጉዳዩ እንግዳ ሳይሆን በተሳካ መንገድ ቀዶ ህክምናውን ማከናወን ችሏል ፡፡

የህጻናቱ እናት ከሳምንት በኋላ ከሆስፒታል እንደምትወጣ ሲነገር ከግማሽ እስከ አንድ ኪሎግራም የሚመዝኑት ህጻናት ግን በልዩ የማቆያ ክፍል ውስጥ ለጥቂት ጊዜ እንደሚቆዩ የህክምና ማዕከሉ ተናግሯል ፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3537580
  • Unique Visitors: 199679
  • Published Nodes: 2652
  • Since: 03/23/2016 - 08:03