ለሴቶች የሚሆን አዲስ የኤች አይ ቪ የመከላከያ ዘዴ ተፈጠረ

ባህር ዳር፡ ሰኔ 12 /2009 ዓ/ም (አብመድ)

ደርባን ውስጥ በተከናወነው 8ኛው የኤድስ ጉባኤ ላይ ሳይንቲስቶች እንደገለጹት ዳፒቪራይን የሚል ስያሜ የተሰጠው እና በሴቶች ብልት የሚቀመጠው የኤአርቪ /ARV/ ቀለበት ሴቶችን ከኤች አይቪ በመከላከል በኩል ትልቅ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

አሁን ባለው መረጃ መሠረት በአፍሪካ ከ15 እስከ 24 ባለው የዕድሜ ክልል ያሉ ሴቶች ለቫይረሱ ተጋላጮች ናቸው፡፡
አሁን እተሰራጨ ያለውን መከላከያ ለመጠቀም ከ4ሺ በላይ እድሜያቸው ከ18 እስከ 45 የሚሆናቸው የደቡብ አፍሪካ, ኡጋንዳ ዚምባብዌ እና ማላዊ ሴቶች ፍላጎት አሳይተዋል፡፡

የሁለት ዓመታት የጊዜ አገልግሎት ያለው ይህ መከላከያ በየወሩ የሚቀየር ነው፡፡

በ2012 የተጀመረው ይህ መከላከያ ዘዴ ብዙውን ጊዜ ከወንድ አጋሮች ጋር ኮንዶም ለመጠቀም በሚያደርጉት ጥረት የሚፈጠረውን አለመግባባት ለማስወገድ አማራጭ ይሰጣቸዋል ተብሏል፡፡

ዲፒቪሪን በሚል የሚጠራው የሲልከን ቀለበት የወሊድ መቆጣጠሪያን የያዘ ሲሆን ጸረ-ኤች አይ ቪ መድሃኒት በመልቀቅ ብልት ውስጥ የገባውን የኤች አይቪ ቫይረስ ይገለዋል ተብሏል::

ምንጭ፡-ሲጅቲኤን

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3527310
  • Unique Visitors: 199328
  • Published Nodes: 2627
  • Since: 03/23/2016 - 08:03