ሁሉም መሥሪያ ቤቶች በአዲሱ የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ሙከራ ትግበራ ላይ ሊካተቱ ነው

ባሕር ዳር፡ሰኔ 06/2008 ዓ/ም(አብመድ)በውስን ተቋማት በሙከራ ትግበራ ላይ የሚገኘው አዲሱ የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ወደ ሙሉ ትግበራ ከመሸጋገሩ በፊት ሁሉም የፌደራልና የክልል መሥሪያ ቤቶች ለሙከራ ትግበራ እንደሚካተቱ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሥራ ምዘና ደረጃ አወሳሰን ጥናት ሰነድ ላይ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል፡፡

በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደርና ሪፎርም ክላስተር አስተባባሪና የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚንስትር ወይዘሮ አስቴር ማሞ በሙከራ ትግበራ ላይ የሚገኘው አዲሱ የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ወደ ሙሉ ትግበራ ከመሸጋገሩ በፊት ሁሉም የፌደራልና የክልል መሥሪያ ቤቶች ለሙከራ ትግበራ ይካተታሉ ብለዋል።

አመራሮችም ሁሉም የፐብሊክ ሰርቪስ ተቋማትና የመንግስት ሰራተኞች እንዲወያዩበት በማድረግ የተሟላ ግንዛቤ ማስጨበጥ እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ በበኩላቸው የስራ ምዘናና የደረጃ አወሳሰን ጥናቱ በርካታ ባለሞያዎች የተሳተፉበትና የውጪ አገራት ተሞክሮዎች የተካተቱበት በመሆኑ የአገሪቱን የሲቪል ሰርቪስ ስርዓት በማዘመን ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ተናግረዋል።

አመራሩ ወጣ ገባና ለእኩል ስራ እኩል ክፍያ ያልነበረውን የደሞዝ አከፋፈል ስርዓት ለመቀየር የተዘጋጀው የስራ ምዘናና የደረጃ አወሳሰን ጥናት የአገሪቱን ሲቪል ሰርቪስ ውጤታማ ለማድረግ ከተቀረጹ ማሻያዎች አንዱ መሆኑን ተገንዝቦ ስራዉን በባለቤትነት መምራት እንደሚገባው ከንቲባው ማስገንዘባቸውን የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ዘግቧል።

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3870103
  • Unique Visitors: 214834
  • Published Nodes: 2859
  • Since: 03/23/2016 - 08:03