ሀገር አቀፍና ክልል አቀፍ ፈተናዎች ከግንቦት 23/2009 ዓ.ም ይጀምራል፡-የክልሉ ትምህርት ቢሮ

ባህር ዳር፡ ግንቦት 18/2009 ዓ/ም(አብመድ)የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ሽብሬ ጆርጋ ለአማራ ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ፈተናው በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ዝግጅት ተደርጓል፡፡ ከፖሊስ ጋርም የፈተና ወቅቱ በሰላም እንዲጠናቀቅ በጋራ እየሰራን ነው፡፡አስፈላጊው ዝግጅትም ተደርጓል ብለዋል፡፡
ወይዘሮ ሽብሬ እንዳሉትም ተማሪዎች ከኩረጃ አስተሳሰብ ነጻ እንዲሆኑ አሳስበው፣ወላጆችም የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡
ሃገር አቀፍና ክልል አቀፍ ፈተናዎች ከግንቦት 23/2009 ዓ.ም ጀምሮ ይሰጣሉ ያሉት ምክትል ቢሮ ሃላፊዋ በተያዘለት ጊዜም ይጠናቀቃል ብለዋል፡፡
ለህብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!!
የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት
አማራ ቴሌቪዥን ፣በአማራ ራዲዮ እና በኤፍኤም ባህር ዳር 96.9 ዜናዎች እና ዝግጅቶች ዙሪያ ለሚኖርዎት ጥቆማና አስተያየት ለአማራ ቴሌቪዥን(ATV)፣ ለአማራ ራዲዮ(AR)፣ ለኤፍኤም ባህር ዳር 96.9 (FM)ለደብረ ብርሃን ኤፍኤም 91.4 (DBFM) ፣ለደሴ ኤፍኤም 87.9(DFM) እና ለበኩር (AB) በማስቀደም በ8200 ማድረስ ይችላሉ::

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3301081
  • Unique Visitors: 189356
  • Published Nodes: 2588
  • Since: 03/23/2016 - 08:03