August 2017

የአውሮፕላን እና የከባድ መኪና ነዳጅ ከቆሻሻ ለሚያመርቱ እንግሊዝ ድጋፍ ልታደርግ ነው

ባህር ዳር፡ ነሀሴ 25/2009 ዓ/ም (አብመድ)የእንግሊዝ የትራንስፖርት ዲፓርትመንት ዝቅተኛ የካርቦን ልቀት ያለው የአውሮፕላንና የከባድ ተሽከርካሪ ነዳጅ ከቆሻሻ ለሚያመርቱ ፕሮጀክቶች የ22 ሚሊየን ፓውንድ ድጋፍ ሊያደርግ መሆኑን ዘ ጋርዲያን ዘገበ ፡፡

 

Amharic

የአፍሪካ ጎብኚዎችን ማበረታታት እንደሚገባ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የንግድ እና ልማት ኤጀንሲ ዋና ጸሃፊ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ባህር ዳር፡ ነሀሴ 25/2009 ዓ/ም (አብመድ)የአፍሪካ መንግስታት የቱሪዝም ዘርፉን ለማስፋፋት ከውጭ ከሚመጡ ቱሪስቶች ይልቅ በአህጉሪቱ ለሚገኙት ጎብኚዎች ትኩረት እንዲያደርጉ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የንግድ እና ልማት ኤጀንሲ ዋና ጸሃፊ ሙክሳ ኪቱይ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Amharic

የኢድ አል አድሀ በዓልን አቅመ ደካሞችን በመርዳት ማክበር ይገባል ተባለ

ባህር ዳር፡ ነሀሴ 25/2009 ዓ/ም (አብመድ)ሕዝበ ሙሰሊሙ የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓልን ሲያከበር አቅመ ደካሞችን በመርዳት ሊሆን እንደሚገባው የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳሰበ።

Amharic

አሜሪካ በሰሜን ኮሪያ ጉዳይ ‹‹ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄዎችን ታስቀድማለች ›› ተባለ

ባህር ዳር፡ ነሀሴ 25/2009 ዓ/ም (አብመድ)ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ‹‹ማውራት ብቻ መልስ አይሆንም ›› የሚል አስተያየት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መልቀቃቸውን ተከትሎ የሃገሪቱ መከላከያ ሴክሬታሪ ጀምስ ማቲስ ከሰሜን ኮሪያ ጋር አሁንም ዲፕሎማሲያዊ መንገዶች አልተዘጉም ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል ፡፡

Amharic

አንድ መቶ ሺ የሳዑዲ የፀጥታ ሃይሎች የሃጅ ስነ ስርዓቱን ከጥቃት ለመከላከል መሠማራታቸውን የሃገሪቱ መንግስት አስታወቀ፡፡

ባህር ዳር፡ ነሀሴ 25/2009 ዓ/ም (አብመድ)በየዓመቱ የሚከበረውን የሃጂ ስርዓት የሚካፈሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የእስልምና አማኞችን ደህንነት ለመጠበቅ ከአንድ መቶ ሺ በላይ የሳዑዲ አረቢያ የጸጥታ ሃይሎች መሰማራታቸውን የሳውዲ አረቢያን መንግስት ምንጭ ጠቅሶ ሲጂቲኤን ዘግቧል ፡፡

Amharic

አልማ በደሴ ዲጅታል ቤተ-መጽሀፍትሊገነባ ነው

ባህር ዳር፡ ነሀሴ 25/2009 ዓ/ም (አብመድ)አማራ አቀፍ ልማት ማህበር /አልማ/ በደሴ ከተማ ዲጅታል ቤተ መጽሀፍት ሊያስገነባ ነዉ;;

   ቤተ መጽህፍቱ የሚገነባዉ በአዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኙ የአልማ አባላት መዋጮ መሆኑ ተገልጿል፡፡

        የከተማ አስተዳዳሩ ምክትል  ከንቲባ አቶ ደሳልኝ በላይ እንደተናገሩት ለቤተ መጸህፍቱ ግንባታ ድጋፍ ላደረጉ የማህበሩ አባላት የሚያደርጉትን ጥረት ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

Amharic

በደቡብ አፍሪካ ሶስት አዛውንቶች ሊጠፋ የተቃረበውን የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውን ለመታደግ እንቅስቃሴ ጀመሩ

ባህር ዳር፡ ነሀሴ 25/2009 ዓ/ም (አብመድ) የእርስዎ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ሊጠፋ ተቃርቧል የሚል መረጃ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቢገለጽ እና ሊጠፉ ከተቃረቡ ቋንቋዎች ዝርዝር ውስጥ ቢካተት ምን አይነት እርምጃ ይወስዱ ይሆን ? በሚል ሃሳቡን ያሰፈረው የቢቢሲ ሪፖርተር በደቡብ አፍሪካ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ለመጥፋት የተቃረበ ሶስት አዛውንቶች ዘመቻ ጀምረዋል ይላል፡፡

 

Amharic

አዲሱን ዓመት በልዩ መልክ ለማክበር ዝግጅት ተደርጓል፡-የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት

ባህር ዳር፡ ነሀሴ 25/2009 ዓ/ም (አብመድ)የኢፌዴሪ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ ቤት ሀላፊ ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ በሰጡት መግለጫ የ2010 አዲስ ዓመትን በልዩ ዝግጅት ለመቀበል የሚያስችለውን መርሀ ግብር ትናንት  ይፋ አድርገዋል።

ዶክተር ነገሪ  “መጪው ዘመን የኢትዮጵያ ከፍታ ነው” በሚል መሪ መልዕክት አዲሱን ዓመት ትቀበላለች ብለዋል።

 

Amharic

ከጋሸና -ሰቆጣ -ላሊበላ እየተገነባ ያለው መንገድ ጥራቱን የጠበቀ አይደለም ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ ፡፡በሂደት ላይ ያለ በመሆኑ ቅሬታ መቅረቡ ተገቢ አይደለም-የመንገዱ የዲዛይን ተቆጣጣሪ

ባህር ዳር፡ ነሀሴ 24/2009 ዓ/ም (አብመድ)ከጋሸና -ላሊበላ- ሰቆጣ ያለው የ189 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታ ከ3.6 ቢሊየን ብር በላይ  ተመድቦለት በሁለት ተቋራጮች አማካኝነት እየተገነባ ይገኛል፡፡

 ይህም ከጋሸና- ላሊበላ -ብልባላ 90 ኪሎ ሜትር  እና ከብልባለ -ሰቆጣ ያለውን 99 ኪሎ ሜትር የሚያጠቃልል ሲሆን ሁለቱም በቻይና ተቋራጮች የሚገነቡ ናቸው ፡፡

Amharic

‹‹የሚጣፍጥ ሁሉ ላይጠቅም ይችላል፡፡ስለሆነም ህዝቡ ሚዲያዎችን መርጦ መጠቀም አለበት ›› ዶክተር ነገሪ ሌንጮ

 ባህር ዳር፡ ነሀሴ 24/2009 ዓ/ም (አብመድ)በግል የሚዲያ ተቋማት ችግርና ስኬቶች ዙሪያ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ የኢፌዴሪ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሀላፊ ሚኒስትር ዶክተር ነገሪ ሌንጮ  አብዛኛዎቹ  የግል ሚዲያዎች ለሰላም ፣ለልማት፣ ለዴሞክራሲ ግንባታ መጠናከር እንዲሁም ለገጽታ ግንባታ የበኩላቸውን ሚና ተጫውተዋል፡፡አንዳንዶች ደግሞ አፍራሽ ሚና ተጫውተዋል ብለዋል፡፡

Amharic

Pages

Visitors

  • Total Visitors: 3406023
  • Unique Visitors: 192810
  • Published Nodes: 2592
  • Since: 03/23/2016 - 08:03