June 2017

የኡጋንዳ ሙዚቀኛ ኪጋላኒ ሲናታሙ የፓርላማ አባል ሆኖ ተመርጠ፡፡

ባህር ዳር፡ ሰኔ 23 /2009 ዓ/ም (አብመድ)የኡጋንዳ ሙዚቀኛ እና የአፍሮ ቢት ኮከብ ሮበርት ኪጋላኒ ሲናታሙ በቅጽል ስሙ ቦቢ ዊን በመካከለኛው የምስራቅ ኡጋንዳ ክፍል በተደረገው የምርጫ ውድድር አሸንፏል፡፡

በምርጫው አራት በግል የሚወዳደሩ ፖለቲከኞችና ተቀናቃኙን በፍጹም  የበላይነት ነው ያሸነፈው ፡፡ በምርጫው ከተሰጠው 33ሺህ ሶስት መቶ ሰላሳ ድምጽ ውስጥ  25ሺህ ስድስት መቶ ሃምሳ ዘጠኙን በማግኘት ነው ያሸነፈው፡፡

Amharic

ዲጂታል የጤና መመርመሪያ መሳሪያዎች ሩቅ በሆኑ አካባቢዎች ፈጣን አገልግሎቶችን መስጠት አስችሎኛል ፡-የዓለም ጤና ድርጅት

ባህር ዳር፡ ሰኔ 23 /2009 ዓ/ም (አብመድ)የዓለማቀፉ የጤና ድርጅት  ዲጂታል የጤና መመርመሪያ መሳሪያዎች በገለልተኛ በሆኑ አካባቢዎች ፈጣን አገልግሎቶችን ለመስጠት አስችሎኛል አለ፡፡

በዚህ በሚቀያየር ዓለም ውስጥ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም አገልግሎቱን ይበልጥ ፈጣን ያደርገዋል የሚለው የአለማቀፉ የጤና ድርጅት ዳብሊው ኤች ኦ ይህም "ነገሮችን" የምናከናውንበትን መንገድ ሊያሻሽል ይችላል ብዙ መንግስታትና ድርጅቶችም አገልግሎቱን ለማስፋት እየሞከሩ ነው ብሏል፡፡

Amharic

በአፍሪካ ውስጥ የሚከሰቱ ግጭቶችን በውይይት መድረክ ለመፍታት ጥረት ለሚያደርጉ አፍሪካውያን እውቅና የሚሰጥ ማክሲ ሳል የሚል ስያሜ የተሰጠው ሽልማት ተመሰረተ

ባህር ዳር፡ ሰኔ 23 /2009 ዓ/ም (አብመድ)በአፍሪካውስጥየሚከሰቱ ግጭቶችን በውይይት መድረክ ለመፍታት ጥረት ለሚያደርጉ አፍሪካውያን እውቅና የሚሰጥ  ማክሲሳልየሚል ስያሜ የተሰጠው ሽልማትበኬንያዋናከተማናይሮቢተመሰርቷል፡፡

Amharic

በሱዳን በአንድ ወር ውስጥ ብቻ የተከሰተዉ የአተት በሽታ 38 ተማሪዎችን ለህልፈተ ህይወት ዳርጓል ፡- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት

ባህር ዳር፡ ሰኔ 23 /2009 ዓ/ም (አብመድ)እንደ ተባበሩት መንግስታት መግለጫ ከሆነ ባለፈውወርብቻ በሱዳን በአጣዳፊ ተቅማጥና ትውኪያ (አተት) በሽታ  38 ሱዳናውያንለህልፈተ ህይወት ሲዳረጉ ከነሃሴ 2016 ጀምሮ በአካባቢው የተከሰተው የአተት በሽታ በድምሩ 317 ሰንችን ህይወት ቀጥፏል፡፡

አሁን በሚዘንበው የክረምት ዝናብ ምክንያት በሽታው ይበልጥ ሊባባስ ይችላል የሚለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአካባቢው አስፈላጊው ጥንቃቄ እና ማህበረሰቡ የግል እና የአካባቢ ንጽህናቸውን መጠበቅ ካልቻሉ ወረርሽኑ ሊቀሰቀስ ይችላል ሲል አስጠንቅቋል፡፡

Amharic

ኬንያ ሁሉን አቀፍ ስሪት ያላቸው የጸረ ኤች አይቪ መድሃኒት በማስገባት ቀዳሚዋ አፍሪካዊት ሃገር ሆነች፡፡

ባህር ዳር፡ ሰኔ 20 /2009 ዓ/ም (አብመድ)በኬኒያ እየተዋወቁ ያሉት የጸረ ኤች አይቪ መድሃኒቶች አደገኛ የጎንዮሽ ጉዳትና ሌሎች የሕክምና ዘዴዎችን የመቋቋም አቅም ያላቸው ሲሆኑ የአሥር ሺህ ሰዎችን ህይወት ሊያራዝም የሚችል መድሃኒት ነው ብለዋል በኬንያን የሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ትምህርት ቤት ዲሬክተር,፡፡

በ 2013 በዩናይትድ ስቴትስ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ የሆነው ይህ መድሃኒት ‹‹ዶሌት ግራት›› የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን በኬንያ ለ 20ሺህ ህሙማን ታካሚዎች እየተሰጠ ነው፡፡

Amharic

የአውሮፓ ሕብረት በሩሲያ ላይ የጣለውን የኢኮኖሚ ማዕቀብ ለ6 ወራት አራዘመ፡፡

ባህር ዳር፡ ሰኔ 21 /2009 ዓ/ም (አብመድ)በዩክሬን ግጭት ላይ ሩሲያ ምታደርገውን ጣልቃ ገብነት ያልወደደው የአውሮፓ ህብረት የኢኮኖሚ ማዕቀብ በሩስያ ላይ ጥሎ የቆየ ሲሆን ህብረቱ ማእቀቡን ለስድስት ወራት ለማራዘም ወስኗል፡፡

የአውሮፓ ምክር ቤት እንደገለጸው በቅርቡ በሩሲያ ጉዳይ ላይ የፈረንሳይ እና የጀርመን መሪዎች በብራሰልስ ከተማ ባካሄዱት ውይይት በሩስያ ላይ የተጣለው ማእቀብ ለስድስት ወራት እንዲራዘም ነው የወሰኑት፡፡

Amharic

አሜሪካ ለሶሪያ አመራሮች ማስጠንቀቂያ ሰጠች

ባህር ዳር፡ ሰኔ 21 /2009 ዓ/ም (አብመድ)የአሜሪካ ባለስልጣናት እንደሚሉት የበሽር አላሳድ መንግስት የኬሚካል የጦር መሳሪያዎችን ለመታጠቁ ሁነኛ ማስረጃዎች አሉን፡፡ ባለፈው ሚያዝያ ላይ የተወሰደው የኬሚካል የጦር መሳሪያዎችን የመምታት ርምጃ በእውቀት ላይ የተመሠረተ ነበር ብለዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት  በሚያዝያ ወር በተፈጸመው ጥቃት ጥቅም ላይ የዋሉ የኬሚካል የጦር መሳሪያዎች አሁንም ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ ሲሉ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል፡፡

Amharic

ዓለም አቀፍ ተቋማት የሳይበር ጥቃት ደረሰባቸው

ባህር ዳር፡ ሰኔ 21 /2009 ዓ/ም (አብመድ)ዓለም አቀፍ የንግድ ተቋማት በሁለት ወር ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የሳይበር ጥቃት ደርሶባቸዋል፡፡

ዋናው የሳይበር ጥቃት በመጀመሪያ በዩክሬን- ኤሌክትሮኒክ ኮምፒተር በአውሮፕላን  የማቆሚያ ስፍራዎች በአውስትራሊያ ውስጥ በካንድ በሪ ቸኮሌት ፕላንት እና በፈረንሳይ ባንክ ቢኤንፒ ፓሪበስ ንብረቶች ላይ ነበር የተከሰተው፡፡

አሁን ደግሞ ባለፈው ማክሰኞ በሳይበር ጥቃት ከተመቱት ውስጥ  የሩሲያ ትልቁ የነዳጅ  ኩባንያ  የዩክሬን ባንኮች እና በርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ይገኙበታል፡፡

Amharic

የህዳሴው ግድብ ውሃ የሚሞላበት ደረጃ ላይ ሲደርስ ሙሌቱን መከወን የሚያስችል ስትራቴጂ ተቀምጧል

ባህር ዳር፡ ሰኔ 21 /2009 ዓ/ም (አብመድ)ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃ የሚመላበት ደረጃ ላይ ሲደርስ ሙሌቱን ለማከናወን ስትራቴጂ ተቀምጦ እየተሰራ መሆኑን የውሃ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር አስታወቀ።

Amharic

ባጃጅ አሽከርካሪዎቹ “ያለኮንትራት አንጭንም” ማለታቸዉን እና ደንበኞችን ለምሬት መዳረጋቸዉንም ቀጥለዋል::

ባህር ዳር፡ ሰኔ 20 /2009 ዓ/ም (አብመድ)በባሕር ዳር ከተማ ሦስት ሺህ 354 ባጃጆች አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ከባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል:: ባጃጆቹ በከተማዉ ህጋዊ ስምሪት እንዲሰጥባቸዉ በተመረጡ 60 የሚደርሱ ፌርማታዎች እና 170 መስመሮች አገልግሎት በመስጠት ከከተማዋ የትራንስፖርት ስምሪት ከ89 በመቶ በላይ ይሸፍናሉ:: ይህም አብዛኛዎቹ ተገልጋዮች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በባጃጆች ላይ እንዲመሰረት አድርጎታል::

Amharic

Pages

Visitors

  • Total Visitors: 3406041
  • Unique Visitors: 192810
  • Published Nodes: 2592
  • Since: 03/23/2016 - 08:03