May 2017

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ህንፃ ሹም ጽ/ቤት በአገልግሎት አሰጣጡ አልተሻሻለም-ተገልጋዮች

ባህር ዳር፡ ግንቦት 23 /2009 ዓ/ም(አብመድ)የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ህንፃ ሹም ጽ/ቤት ከጥልቅ ተሃድሶ እንቅስቃሴ በኋላም በአገልግሎት አሰጣጡ መሻሻል እንዳላሳየ ተገልጋዮች ተናገሩ፡፡

          የባለሙያ እና ግብዓት እጥረቶች አገልግሎቱ ፈጣን እንዳይሆን ምክንያት ተብለው ተጠቁመዋል፡፡

ተገልጋዮች ለአማራ ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ጉዳያችንን ስናመጣ ‹‹ቆይ እገሌ ይፈርምልህ፣ሀላፊው ወይም ሀላፊዋ የለችም፣በዚህ ቀን ና ይሉሃል በቀኑ ስትመጣም አይገኙም ብለዋል፡፡

Amharic

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት 12ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በአልን ለማክበር የቅድመዝግጅት ስራውን በተያዘለት ጊዜ እየሰራ መሆኑን አስታውቀ፡፡

ባህር ዳር፡ ግንቦት 22 /2009 ዓ/ም(አብመድ) 12ኛው የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን የሚዘጋጅበት የአፋር ብሄራዊ ክልል በሰመራ ከተማ ለዝግጅቱ የሚረዱ መሰረተ ልማቶችን እያከናወነ ነው፡፡ 
የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን ዝግጅት ኮሚቴ አስተባባሪ አቶ መሃመድ አወል እንደሚሉት

Amharic

ኬኒያ የመሪነት ስፍራዋን በጎረቤቷ ኢትዮጵያ ተነጠቀች

ባህር ዳር፡ ግንቦት 23 /2009 ዓ/ም(አብመድ) ኬኒያ ለረጂም ጊዜ በምስራቅ አፍሪካ የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት ሆና ብትቆይም አሁን ግን በጎረቤቷ ኢትዮጵያ የመሪነት ቦታዋን እየተነጠቀች መሆኗን አይ ኤም ኤፍ ገለጸ
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ ቀመር እንደሚያሳየው የኢትዮጵያ አጠቃላይ ዓመታዊ ገቢ ( ጂዲፒ ) እስከዚህ ዓመት መጨረሻ ድረስ 78 ቢሊዮን ዶላር ይሆናል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ባለፈው ዓመት 72 ቢሊዮን ዶላር አመታዊ ገቢ ማስመዝገቧን ጠቅሷል ፡፡ 

English

ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በህገወጥ መንገድ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ወደሃገራቸው እየገቡ ነው

ባህር ዳር፡ ግንቦት 22 /2009 ዓ/ም(አብመድ) የሳውዲ አረቢያ መንግስት ህጉን ሊቀይር ይችላል የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ በመያዝ እስካሁን ለመምጣት ፍላጎት ያላሳዩ ወንድም እና እህቶች ክብር እና መብታቸው ሳይደፈር ወደ ሃራቸው እንዲመለሱ ተመላሾቹ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አሚነት የሱፍ ከዛሬ 6 ዓመት በፊት ያደገችበትን ኮምቦልቻ ከተማን ለቃ በህገወጥ መንገድ ወደ ሳውዲ አረቢያ በማቅናት ከፖሊስ እየተደበቀች ተሳቃ ስትሠራ መቆየቷን ተናግራለች ፡፡
አሁን ግን የሳውዲ መንግስት የውጭ ዜጎች ሃገሩን ለቀው እንዲወጡ ያስተላለፈውን ትእዛዝ ተቀብላ በኢትዮጵያ መንግስት ድጋፍ ወደ ሃገሯ መመለሷን ገልጻለች፡፡

English

ዛንዚባር የኮሌራ ወረርሽኝን ለመከላከል የመንገድ ላይ ምግብ ሽያጭን ከለከለች፡፡

ባህር ዳር፡ ግንቦት 22 /2009 ዓ/ም(አብመድ) በዛንዚባር ከፊል ደሴቶች ላይ ከባድ ዝናብ ጥሎ የተፈጠረው ጎርፍ የንጽህና ችግር አስከትሎ ኮሌራ በመቀስቀሱ ምክንያት የመንገድ ላይ ምግቦች እንዳይሸጡ መንግስት ክልከላ ማድረጉን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡

English

ለ17 ኣመታት የጓጉለትን ያህል በ6 ህጻናት ተካሱ

ባህር ዳር፡ ግንቦት 20/2009 ዓ/ም(አብመድ)አዴቦዬ እና አጂቦላ ታይዎ ትዳር መስርተው ለ17 ዓመታት ልጅ ለማግኘት ቢመኙም ሳይሳካላቸው ቆይቶ ሰሞኑን በአንድ ጊዜ የ3 ሴትና የ3 ወንዶች ወላጆች መሆናቸውን ሲኤንኤን ዘግቧል ፡፡

በአሜሪካ- ሪችሞንድ ቨርጂኒያ ኮመንዌልዝ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ማዕከል ከ30 ሳምንታት እርግዝና በኋላ በቀዶ ህክምና የተገላገለችው ናይጄሪያዊቷ አጂቦላ ታይዎ እና ባለቤቷ ልጅ ወልዶ ለመሳም ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖራቸውም ባለመሳካቱ ተስፋ ወደመቁረጥ ተቃርበው እንደነበር ተናግረዋል ፡፡

English

ለጋራ ችግር የጋራ መፍትሄ ያስፈልጋል ህዝቡ አብሮን ሊሰራ ይገባል፡-የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ሀላፊዎች

ባህር ዳር፡ ግንቦት 20/2009 ዓ/ም(አብመድ)የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር በከተሞች መድረክ ዝግጅት ከህብረተሰቡ ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ ሰጥቷል፡፡አቶ ሙላት መንግስቴ ከከንቲባ ጽ/ቤት ትራንሰፖርትን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት  ወደ 420 ባጃጆች አሉ ቀን እማናገኛቸው ሌሊት የሚሰሩ ተደብቀው የሚውሉ አሉ፡፡ህብረተሰቡም ቢጠቁም  ጥሩ ነው፡፡ስርቆትና ዝርፊያም እንዳለ እንሰማለን ግን ከጸጥታ ባለሙያዎች ጋር እየሰራን ነው፡፡

English

Pages

Visitors

  • Total Visitors: 3527298
  • Unique Visitors: 199328
  • Published Nodes: 2627
  • Since: 03/23/2016 - 08:03