4ኛው የኢትዮጵያ የታዳጊዎች የአትሌቲክስ ሻንፒዮና በአማራ ክልል አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

ባህር ዳር፡ ሰኔ 13 /2009 ዓ/ም (አብመድ)በኦሮሚያ ክልል በአሰላ ከተማ ከሰኔ7- 11/2009 ዓ/ም ሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም 22 የአትሌቲክስ ክለቦች በውድድሩ ተሳትፈዋል፡፡

713 አትሌቶች የተካፈሉበት ውድድር አላማው ከፈረንጆቹ ሃምሌ 12 -16 /2017 በኬንያ ናይሮቢ ለሚደረገው 10ኛው የአለም ታዳጊዎች ሻንፒዮና ሀገራቸውን የሚወክሉ አትሌቶችን ለመምረጥ ነው፡፡ በተጨማሪም ተስፈኛ ተተኪ አትሌቶች የታዩበት እነደነበርም የውድድሩ አዘጋጆች ተናግረዋል፡፡

በዚህ ውድድር የተሳተፈው የአማራ ክልል የአትሌቲክስ የልኡካን ቡድን ውድድሩን የበላይነት አሸንፏል ፡፡ በድምሩ 191 ነጥብ በማስመዝገብ፡፡

በቅርብ ጊዜ እየተጠናከረ የሚገኘው ሲዳማ ቡና አትሌቲክስ ክለብ በ 177 ነጥብ 2ኛ ፤ ኦሮሚያ ክልል በ155 ነጥብ 3ኛ ሆነው ውድድራቸውን አጠናቀዋል፡፡

ውድድሩን በበላይነት ያጠናቀቀው የአማራ ክልል የአትሌቲክስ የልኡካን ቡድን ነገ ወደ ባ/ዳር እንደሚመለስ የክልሉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ አማካሪ በስልክ ለአማራ ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

ግርማ ሞገስ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3870250
  • Unique Visitors: 214838
  • Published Nodes: 2859
  • Since: 03/23/2016 - 08:03