37ኛውን የኢህዴን /ብአዴን/ የምስረታ በአልን ስናከብር የአላማ ጽናታችንን በማደስና ጥልቅ ተሃድሶውን በማጠናከር መሆን እንደሚገባው የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለምነው መኮንን ተናገሩ፡፡

ባህር ዳር: ህዳር 11/2010(አብመድ) ከፍተኛ ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች በባህር ዳር ከተማ የሰማዕታት ሃውልት ስር በአማራ ክልል ፖሊስ ማርሽ ባንድ በመታጀብ የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ ሰማዕታቱን አስበዋል፡፡

በዕለቱ የተገኙት የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለምነው መኮንን እንዳሉት የምስረታ በአሉን ስናከብር የአላማ ጽናታችንን በማደስ እና የተጀመረውን ጥልቅ ተሃድሶ በማጠናከር መሆን ይገባዋል ብለዋል፡፡
ታጋዮች ሰላም እና ዲሞክራሲን ለማስፈን ምትክ የለሽ ህይወታቸውን ሰውተዋል ያሉት አቶ አለምነው የታጋዮችን ቁርጠኝነት በመላበስ አላማቸውን ለማስቀጠል የአሁኑ ታጋዮች ርብርብ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡
የብአዴን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ከበደ ጫኔ በበኩላቸው በታጋዮች መስዋዕትነት አሁን ለተደረሰበት የልማት እና ዴሞክራሲ ግንባታ ደርሰናል ብለው አካል ጉዳተኛ እና አቅመ ደካማ ታጋዮችም ሊታሰቡ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
37ኛው የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ብአዴን/የምስረታ በአል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው፡፡
ሪፖርተር ፡-አወቀ ካሴ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3527339
  • Unique Visitors: 199328
  • Published Nodes: 2627
  • Since: 03/23/2016 - 08:03