2 ኛው የቻይና-አፍሪካ -ኢንቨስትመንት ፎረም በሞሮኮ በቅርቡ ይካሄዳል፡፡

ባህር ዳር: ህዳር 13/2010(አብመድ)የሞሮኮ ዋና ከተማ ማራካሽ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ህዳር 27 እና 28 ለሚካሄደው ሁለተኛው የቻይና-አፍሪካ የኢንቨስትመንት ፎረምን ለማስተናገድ ዝግጅቷን ማተናቀቋን አስታውቃለች፡፡

ፎረሙ ከ 400 በላይ የቻይና እና የአፍሪካ የንግድ መሪዎችን ያገናኛል፡፡
አዘጋጆቹ ባስተላለፉት መግለጫ መሰረት ፎረሙ የቻይና-አፍሪካ የኢኮኖሚ ትብብር ሙሉ በሙሉ እንዲሳካ አስፈላጊ ሁኔታዎችን የሚፈጥር ይሆናል፡፡ በቻይና እና በአፍሪካ ሀገራት መካከል ባሉ ዋና ዋና ባለድርሻ አካላት መካከል የንግድና የኢንቨስትመንት ግንኙነቶች እንዲካሄዱ በተለይም በኢንዱስትሪ ዘርፍ ከፍተኛ እሴት ያላቸውን እና እሴት የተጨመሩ ባቸውን እቃዎች በማምረቱ በኩል ዘላቂ ትብብር ለማጎልበት የሚያስችሉ የንግድ ግንኙነቶች እንደሚኖሩ ያስችላል ሲል መግለጫው አመልክቷል፡፡

ፎረሙ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን የውይይት መድረኮቹ እና ክርክሮቹ በአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ እሴቶች ላይ ያለውን ተፅዕኖ እና አህጉሩን እውነተኛ የኢንዱስትሪ መድረክ እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የቻይና እና አፍሪካን የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች እና የሥራ አካባቢዎችን ለመረዳት የሚረዱ ጠቃሚ አስተያየቶች የሚቀርብባቸው ተግባራዊ አውደ ጥናቶች ይሆናሉም ተብሏል፡፡

በ 2016 ከ 122 ቢሊዮን ዶላር በላይ በንግድ እና 2.5 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ ቀጥተኛ ያልሆነ ኢንቨስትመንት ልውውጥ በሁለቱ መካከል የተደረገ ሲሆን ቻይና በአሁኑ ጊዜ የአፍሪካ ዋንኛ የንግድ አጋር መሆኗንም አረጋግጣለች፡፡

ቻይና በአህጉሪቱ ጥሩ እንቅስቃሴ እያሳዩ የሚገኙ ከ10ሺህ በላይ ኩባንያዎች አሏት፡፡ እንዲሁም ከአፍሪካ ጋር ያለው የንግድ ግንኙነት በ2016 -190 ቢሊዮን ዶላር ሲደርስ ከህንድ፣ ከፈረንሳይ እና ከአሜሪካ ጋር ሲነጻጸር አብላጫውን ይዟል አፍሪካ ኒውስ እመንደዘገበው፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3693147
  • Unique Visitors: 209286
  • Published Nodes: 2809
  • Since: 03/23/2016 - 08:03