ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ከቻይና የኢንቨስትመንት ልዑካን ቡድን ጋር ተወያዩ

ባህር ዳር፡ ሐምሌ 27/2009 ዓ/ም (አብመድ)ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከስድስት የቻይና ኩባንያዎች የተውጣጡ የቢዝነስ ልዑካንን ዛሬ በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ልዑካን ቡድኑ “ተች ሮድ ኢንተርናሽናል ሆልዲንግ ግሩፕ” የተሰኘ የቻይና ድርጅት ሊቀመንበር በሆኑት ሚስተር ሂ ሊየሁይ እየተመራ ነው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች የመከረው፡፡

11 የልኡካን ቡድኑ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ባደረገው ውይይት በኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።

ከደረቅ ቆሻሻ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨትና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት በሚገኙበት አካባቢ በዝቅተኛ ወጪ ቤቶችን ለመገንባት እቅድ እንዳላቸውን ነው የጠቀሱት፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ልዑካን ቡድኑ ያቀረበው ሀሳብ ሀገሪቱ ከያዘቻቸው የትኩረት መስኮች ጋር የሚስማማ በመሆኑ ማልማት እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡

መንግሥትም በሚሰማሩበት የኢንቨስትመንት ዘርፍ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ መግለፃቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ኤፍ ቢ ሲ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3527287
  • Unique Visitors: 199328
  • Published Nodes: 2627
  • Since: 03/23/2016 - 08:03