ጎንደር የቱሪዝም ከተማ እንደሆነችው ሁሉ የኢንቨስትመንት ተመራጭ ከተማም እየሆነች ነው፡፡የተመረቀው የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክትም ለከተማዋ እድገት ጥሩ አጋጣሚን ይፈጥራል፡-ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

ባህር ዳር: ህዳር 11/2010(አብመድ)11ኛው ሀገር አቀፍ የውሃ አገልግሎቶች ፎረም ‹‹ለአየር ንብረት ለውጥ ተስማሚ የሆነ ዘላቂ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ለከተሞች!›› በሚል መሪ መልዕክት በጎንደር ከተማ ዛሬ ተጀምሯል፡፡Image may contain: 1 personበስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው‹‹ዛሬ የተመረቀው የጎንደር ንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የከተማውን የ44 በመቶ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ወደ 100 በመቶ ያደርሰዋል፡፡ስለሆነም የጎንደርን አንዱን ችግር ቢያንስ ዘግይተንም ቢሆን ፈትተናል፡፡ከእንግዲህ በኋላ የከተማዋ ችግር ተደርጎ ይነሳ የነበረው የው አቅርቦት ጉዳይ ተፈቷል ››ብለዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም ለበርካታ ጊዚያት ሲነሳ የነበረውን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እንዲፈታ የተሳተፋቸሁ በሙሉ ምስጋና ይገባችኋል ብለው የነበረውን ውስን የውሀ መጠን ለሁሉም እንዲዳረስ በትኩረት ለሰሩት የከተማ አስተዳደሩ አመራሮችና ውሃ አገልግሎት ሰራተኞች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አቶ ገዱ አክለውም ‹‹ከሁሉም በላይ ግን የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በትዕግስት ስለጠበቃችሁን ምስጋና ይገባችኋል፡፡››
ጎንደር የቱሪዝም ከተማ ነች፡፡የኢንቭስትመንት ተመራጭ ከተማም እየሆነች ነው፡፡በቀጣይም ኢንቨስትመንቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በጋራ እንሰራለን ብለዋል፡፡
Image may contain: 1 person, suit

የኢፌዴሪ ውሃ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅኔር ስለሺ በቀለ በበኩላቸው የጎንደር ከተማ አስተዳደር የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ከግብ እንዲደርስ የኢትዮጵያ መንግስት ፣ዓለም ባንክ ፣አማራ ክልል እና የጎንደር ከተማ አስተዳደር ትልቁን ድርሻ ወስደዋል፡፡ በቀጣይም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ላይ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡

በሀገሪቱም 62 ሚሊዮን ህዝብ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽ ሆኗል፡፡ከዚህም ውስጥ 10 ሚሊዮን የሚሆኑት በከተማ የሚኖሩ ነዋሪዎች ናቸው፡፡
በ2017 ሀገሪቱ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ለመሰለፍ በምታደርገው መጠነ ሰፊ ጥረት የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነት ልዩ ትኩረትም ተሰጥቶታል ብለዋል፡፡

ለረዥም ዓመታት በውሀ አቅርቦት ላይ ተቸግረን ነበር፡፡አሁን ላይ የጎንደር ከተማ አስተዳደር የነበረበትን የውሃ አቅርቦት ችግር ይፈታልናል፡፡የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ እውን እንዲሆን ለተሰተፉ በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተቀባ ተባባል፡፡
ከ561 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የሆነበትን የጎንደር ንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት አገልግሎት ላይ የዓለም ባንክ በድጋፍና በብድር በኩል ተሳትፎ አድርጓል፡፡

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ፣ሱዳንና ደቡብ ሱዳን የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ወይዘሮ ካሮሊን ተርክ ‹‹የዓለም ባንክ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ትኩረት ሰጥቶ ድጋፍ ያደርጋል፡፡የጎንደር ንጹህ ውሃ መጠጥ ፕሮጀክትም አንዱ አካል ነው፡፡ግንባታው ከፍተኛ የመፈጸም አቅም የታየበት ፕሮጀክት ነው ብለዋል፡፡Image may contain: 1 person, suit

የክልሉ መንግስትና ኢፌዴሪ ውሃ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር ለውሃ ፕሮጀክቱ መጠናቀቅ ከዓለም ባንክ ጋር በመሆን ትልቅ ስራ ሰርታችኋል፡፡በቀጣይም በመቀሌ ፣ሀዋሳ እና ጅማ በሚኖሩን ፕሮጀክቶች በጋራ እንሰራለን ብለዋል፡፡የዓለም ባንክም በጥቅሉ በ23 ከተሞች ላይ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች አሉት ስለሆነም ተጠናቀው ለህዝቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ከመንግስት ጋር በጋራ እንሰራለን ብለዋል፡፡
የጎንደር ንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በ2006 ዓ/ም ነበር ወደ ግንባታ ስራ የገባው፡
ፎረሙ እስከ ህዳር 13/2010 ይቀጥላል፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3284044
  • Unique Visitors: 188936
  • Published Nodes: 2588
  • Since: 03/23/2016 - 08:03