ግብፅ ብረት ላይ ተጨማሪ ታሪፍ ጣለች

ባህር ዳር፡ ግንቦት 30 /2009 ዓ/ም(አብመድ)ግብፅ የሃገር ውስጥ ምርቷ የሆነውን ብረት ከገበያ ውድቀት ለመታድ  እና የአካባቢውን የብረት አምራቾች ለመጠበቅ

ከውጪ በሚገባው የብረት ምርት ላይ ተጨማሪ ታሪፍ ጥላለች፡፡

ግብፅ ጊዜያዊ የታሪፍ ጭማሪ ያደረገችው ከቻይና፣ቱርክ እና ዩክሬን በሚገባው ብረት ላይ  መሆኑን አል-አህራም ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

ከውጪ በአማራጭነት የሚገቡ ምርቶች በአካባቢው ምርት እና አምራቾች የሚደርሰውን ኪሳራ ለመቀነስ ብሎም ለመከላከል ነው ብሏል ጋዜጣው፡፡Image result for egypt iron

 የታሪፍ ጭማሪው በቻይና ብረት ላይ 17 በመቶ በቱርክ ብረት ከ10-19 በመቶ እና በዩክሬን ብረት ላይ ደግሞ ከ15-27 በመቶ ጭማሪ እንደሚደረግ ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

የግብፅ የንግድ ሚኒስቴር ባወጣው ሪፖርት እንዳለው ግብጽ ውስጥ በተደረገው ጥናት  ከውጭ በአማራጭነት የሚገባው የብረት ምርት ከአካባቢው አምራቾች ምርት ጋር መወዳደር ባለመቻሉ ሲሆን ከአምራቾች በተሰበሰበ መረጃ የውጭ ምርቱ በሃገር ውስጥ ምርቱ ላይ ተጽኖ እየፈጠረ እንደሆነ የተሰበሰበው ቅሬታ አመልክቷል፡፡

ሽንዋ እንደዘገበው ከሆነ ውሳኔው ለአራት ወራት የሚቆይ ሲሆን የህጉ አስገዳጅነት መቸ እንደሚፈጸም ግን ሪፖርቱ ያለው ነገር የለም፡፡

ምንጭ፡-አልሃራም ጋዜጣ እና ሽንዋ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3870094
  • Unique Visitors: 214834
  • Published Nodes: 2859
  • Since: 03/23/2016 - 08:03