የ102 አመቷ ኬንያዊት ዛሬ በተካሄደው ምርጫ ድምጻቸውን ሰጡ

ባህር ዳር፡ ነሀሴ 2/2009 ዓ/ም (አብመድ)የ102 ዓመቷ ሊዲያ ጋቶኒ በኬንያ ምርጫ በመራጭነት ተሳተፉ፡፡ወይዘሮ ሊዲያ ትናንት ምሽት የኬንያ ቀጣይ እጣፈንታ ይመለከተኛል በማለት ሰልፉን ከምንም ሳይቆጥሩ ቀድመው በመገኘት ድምጻቸውን ይወክለኛል ላሉት ተመራጭ ፕሬዝዳንት ሰጥተዋል፡፡

ወይዘሮ ሊዲያ ከመረጡ በኋላ ‹‹ምርጫውን አሸንፎ ሀገሪቱን የሚመራው ቀጣይ የኬንያ መሪ የጠቢቡ ሰለሞንን የመሪነት ጥበብ ይስጠው፡፡ሀገሪቱንም ፈጣሪ ይጠብቃት ››ብለዋል፡፡

1915 እኤአ ወደዚህ ዓለም የመጡት ወይዘሮ ሊዲያ የኬንያ ነጻነት አባት ተብለው የሚጠሩትንና የመጀመሪያውን የኬንያ ፕሬዝዳንት ጀሞ ኬንያታ አድናቂ ሲሆኑ በዛሬው ምርጫም ልጃቸው ኡሁሩ ኬንያታ ቢያሸንፍ እንደሚወዱ ሳይሸሽጉ ፍላጎታቸውን ተናግረዋል፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3537651
  • Unique Visitors: 199679
  • Published Nodes: 2652
  • Since: 03/23/2016 - 08:03