የፀጥታው ምክር ቤት ላይቤሪያ ያካሄደችውን ሰላማዊ ምርጫ አደነቀ፡፡

ባህርዳር፡ጥር 03 /2010 ዓ/ም(አብመድ)የቀድሞው የእግር ኳስ ተጫዋች ጆርጅ ዊሃን አዲስ ፕሬዝዳንት አድርጎ የተጠናቀቀው የላይቤሪያ ምርጫ ምንም ችግሮች ሳይታዩ ፕሬዝዳንታዊ ሽግግር መደረጉ የህዝቡን የዲሞክራሲ ግንዛቤ ዕድገት ያሳያል ሲል በተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ማድነቁን አፍሪካ ኒውስ ዘገበ ፡፡

የላይቤሪያ ህዝብ እና መንግስት ብሎም የፖለቲካ መሪዎች፣የሲቪል ማህበረሰቡና የመገናኛ ብዙሃን ለዚህ ሰላማዊ ሽግግር ትልቅ ሚና ስለተጫወቱ ‹እንኳን ደስ ያላችሁ › ተብለዋል ፡፡

ተወዳዳሪ እጩዎቹ ጆርጅ ዊሃ እና ተሰናባቹ ምክትል ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ቦአካይ ሃላፊነት የተሞላበት  የምርጡኝ ዘመቻ ማካሄዳቸው ለሌሎች አብነት እንደሚሆን ሲገለጽ የቀድሞዋ ፕሬዝዳንት የኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ ጉልህ ሚና ተጫውተዋል በሚል ምክር ቤቱ ሽልማት ሰጥቷል፡፡

የፀጥታው ምክር ቤት አባላት ለምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ /ኢኮዋስ/፣ለአፍሪካ ህብረት እና ለሁሉም የዓለም አቀፍ፣የክልላዊ እና የሀገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢ ልዑካን ለምርጫው ሂደት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን ገልፀዋል ፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3872490
  • Unique Visitors: 214892
  • Published Nodes: 2859
  • Since: 03/23/2016 - 08:03