የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፈጠራ ስራ ባለቤቶች በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሽልማት ተበረከተላቸው::

ባህር ዳር: ህዳር 12/2010(አብመድ)የፈጠራና የምርምር ሰዎችን በማበረታታት የሀገሪቱን ቴክኒሎጂ ወደፊት አንድ አርምጃ የሚያራምድ ሀገር አቀፍ የሳይንስና ቴክኖሎጂ የሽልማት ስነስርዓት በአዲስ አባባ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ጥቅምት 8 ና 9/2010 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡Image may contain: one or more people and indoor

በዚህ የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባዘጋጀው የሽልማት ፕሮግራም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአራት የወርቅ ሜዳሊያዎች ባለቤት ለመሆን በቅቷል፡፡

በአዳዲስ የፈጠራ ስራዎችና ምጡቅ ሀሳቦች የወርቅ ሜዳሊያ ሽልመት የተበረከተላቸው የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችና ስታፍ አባላት ዶ/ር ሳሙኤል ሳህሌ፣ አቡሃይ ውብሸት፣እመቤት ክብካብና አዚዛ ኡመር ናቸው፡፡የፈጠራ ባለቤቶቹ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር የተከበሩ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝና ከኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ እጅ የሜዳሊያ ሽልማቶቹ ተበርክቶላቸዋል፡፡Image may contain: 4 people, people smiling, people standing and outdoor

የፈጠራ ባቤቶቹን ለሽልማት ያበቋቸው ዝርዝር ስራዎችን በተመለከተ ፣ዶ/ር ሳሙኤል ሳህሌ የድህረ ምረቃ ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ፣ከዳጉሳ ቢራ በመስራት እንዲሁም የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪ የሆነው አቡሃይ ውብሸት የላፕቶፕ ባትሪ መሙያ ኬሚካል፣ የመጸዳጃ ቤት ሽታ ማስወገጃ ኬሚካልና ሌሎች ፈጠራዎችን በመስራት ሲሆን እነዚህ ፈር ቀዳጂ ስራዎች ሀገራችን ለያዘችው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሽግግር ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ይታመናል፡፡

ሌሎች የዩኒቨርሲቲው የፈጠራ ባለቤቶችና የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪ የሆኑት ማለትም እመቤት ክብካብ የብረት ዝገት ማስወገጃ/Anti-rust/ ኬሚካል ስትሰራ፣ ሌላኛዋ አዚዛ ኡመር ደግሞ የድጅታል ማስታዎቂያ ሰሌዳ በመስራት ከብዙ የግልና የመንግስት የፈጠራ ተወዳዳሪዎች መካከል ጎልተው ድንቅ የፈጠራ ስራዎቻቸውን አሳይተዋል፡፡

ምንጭ፡-የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3693160
  • Unique Visitors: 209288
  • Published Nodes: 2809
  • Since: 03/23/2016 - 08:03