የዓለማችን ሞቃታማው ሥፍራ በረዶ ታየበት

ባህርዳር፡ጥር 02 /2010 ዓ/ም(አብመድ)በአሁኑ ወቅት ዓለማችን አስገራሚ የአየር ሁኔታ እየተፈራረቀባት መሆኑ ከየስፍራው ቢዘገብም ሰሞኑን የዓለማችን ሞቃታማው ክልል በበረዶ መሸፈኑ ግን ይበልጥ ግርምትን መጫሩን ሲ ኤን ኤን አስነብቧል ፡፡Image may contain: sky, mountain and nature

ዓይን ሴፍራ እየተባለች በምትጠራውና ‹ የሰሃራ መግቢያ በር › በሆነችው የአልጄሪያ ከተማ ከ40 ዓመታት ወዲህ ታይቶ የማያውቅ 15 ኢንች በረዶ መከመሩን አንዳንድ የዜና ምንጮች ቢዘግቡም የአካባቢው ባለስልጣናት ግን መጠኑ እንደሚያንስ ተናግረዋል ፡፡

ምንም እንኳ የሰሃራ በረሃ የሌሊቱ የአየር ሁኔታ ከአስር ዲግሪ ሴልሺየስ ወርዶ ያልተለመደ በረዶን ለጥቂት ጊዜ ማቆየት ቢችልም የአሁኑ ክስተት ግን ለአንድ ቀን ያህል በመቆየት በርካቶችን አስደንቋል ፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3527360
  • Unique Visitors: 199328
  • Published Nodes: 2627
  • Since: 03/23/2016 - 08:03