የኬንያ ፍርድ ቤት በድጋሚው ምርጫ ላይ ሌሎቹም እንዲካተቱ ለምርጫ ቦርዱ ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡

ባህር ዳር፡ ጥቅምት 2/2010 ዓ/ም (አብመድ)የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በድጋሚ በሚከናወነው ፕሬዝዳንታዊው ምርጫ ውድድር ላይ ሌሎች ተፎካካሪዎችን እንዲያካትት ለምርጫ ቦርድ ትዕዛዝ ማስተላለፉን አፍሪካ ኒውስ ዘገበ ፡፡ 

የምርጫ ቦርዱ በድጋሚ በሚከናወነው ምርጫ ላይ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታን እና ዋነኛ ተቀናቃኛቸው ራይላ ኦዲንጋ በድጋሚ ለመወዳደር እ.ኤ.አ. ለጥቅምት 26 /2017 ቀነ ቀጠሮ ይዞ በመጠባበቅ ላይ እንደነበር ተዘግቧል፡፡

የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተከትሎ ባለፈው ነሐሴ በተከናወነው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከ1 በመቶ ያነሰ ውጤትን ያስመዘገቡት ኢኩሩ ኡኮት በድጋሚ በሚከናወነው ምርጫ በአዲስ መንፈስ እንደሚወዳደሩ ገልጸዋል፡፡

ምንም እንኳን ዋነኛው የኡሁሩ ኬኒያታ ተቀናቃኝ ራይላ ኦዲንጋ ከምርጫው ራሳቸውን ቢያገሉም ፕሬዝዳንቱ ከሌሎች ተወዳዳሪዎቻቸው ጠንካራ ፉክክር ሊገጥማቸው እንደሚችል እየተዘገበ ነው፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3433600
  • Unique Visitors: 194891
  • Published Nodes: 2605
  • Since: 03/23/2016 - 08:03