የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የኢትዮጵያና ኩባ ወዳጅነት የበለጠ ሊጎለብት እንደሚገባው ተናገሩ፡፡

ከኩባው ፕሬዝዳንት ራውል ካስትሮ በተደረገላቸው ግብዣ መሰረት ዶክተር ሙላቱ በሀገሪቱ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡Image may contain: 2 people
ዶክተር ሙላቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የላቀ አስተዋጽኦ ባደረጉ ኩባውያን መታሰቢያ ላይ የአበባ ጉንጉን ካስቀመጡ በኋላ ለኢትዮጵያ ነጻነት ህይወታቸውን አሳልፈው የሰጡ ኩባውያን ወታደሮችን አስበዋል፡፡

ትናንት ሃቫና የገቡት ዶክተር ሙላቱ ኩባውያን በጸረ አፓርታይድ ትግሉ ያበረከቱትን አስተዋጽኦም አድንቀዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ሙላቱ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መልካም የሚባል መሆኑን ገልጸው የኢንቨስትመንትና ሌሎች የትብብር መስኮቻቸውን ማስፋት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡Image may contain: 2 people, people standing, flower and outdoor

ሁለቱ ሀገራት በጤና እና ግብርና መስኮች የመሰረቱትን ጠንካራ ትብብር በትምህርትና ባዮቴክኖሎጂ ዘርፎች ሊደግሙት እንደሚገባም ነው የተመለከተው፡፡

የኩባ ሪፐብሊክ ተዋጊዎች ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት ዴልሳ ኤስተር ፐዬብላ በበኩላቸው ሁለቱ ሀገራት አንድነታቸውንና የህዝቦቻቸውን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ያደረጉት ጥረት የጠንካራ ግንኙነታቸው ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡Image may contain: 12 people, people standing, suit and outdoor

ፕሬዝዳንቱ ሁለቱ ሀገራት በትምህርት፣ በጤናና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚችሉባቸው መንገዶች ዙሪያ ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ይወያያሉ።

ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የኩባ ጉብኝታቸውን ጥር 4/2010 እንደሚያጠናቅቁም ነው ፕረንሳ ላቲና በድረ ገጹ ያስነበበው፡፡

 

ኢዜአ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3537551
  • Unique Visitors: 199679
  • Published Nodes: 2652
  • Since: 03/23/2016 - 08:03