የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ጥምረት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተለያዩ አካላት ጋር በመቀናጀት አፍሪካን ከተፈጥሮ አደጋ ቀድሞ መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ በባህርዳር ከተማ እየመከሩ ነው፡፡

ባህር ዳር፡ መስከረም 29/2010 ዓ/ም (አብመድ)የዓለም የቀይ መስቀል ማህበር፣የዓለም የምግብ ድርጅት፣የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ጥምረት በጋራ የሚያካሂዱት ጉባዔ በአፍሪካ የተፈጥሮ አደጋዎች ዙሪያ ተነጋግሯል፡፡

ጉባዔው በአፍሪካ ያጋጠሙ የጎርፍ አደጋዎችን፣የመሬት መንቀጥቀጥን እና የድርቅ አደጋን በተመለከተ ውይይት ተደርጎባቸው የመፍትሄ ሃሳብ ተቀምጦላቸዋል፡፡Image may contain: one or more people, people sitting, table and indoor
ቀድሞ መከላከል፣አማራጭ ማዘጋጀት፣የተፈጥሮ ክስተትን ቀድሞ መገመት እንደሚገባ በጉባኤው ተመላክቷል፡፡

በኢትዮጵያ በኩል የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ጥናቶች አቅርቧል፡፡በ 2007/2008 ዓ.ም. የተከተሰተው ኤልኒኖ እና በጣና ሀይቅ ላይ የተከሰተው የእንቦጭ አረም ወረራን በተመለከተ ጥናቶች ቀርበዋል፡፡

በተለይ በእንቦጭ አረም ላይ እስካሁን የተሰራው ምርምር አመርቂ አይደለም፡፡በመሆኑም የአፍሪካ ህብረት ሀገራት እና ዩኒቨርሲቲዎች ሳይንሳዊ መፍትሄዎችን በፍጥነት ማምጣት እንደሚገባቸው ሀሳብ ተነስቷል፡፡

እንቦጭ አረም ቀደም ብሎ በቪክቶሪያ ሀይቅ ሲከሰት በእጅ ከመንቀል ጀምሮ በኬሚካል እስከ ማጥፋት የመፍትሄ እርምጃ ተወስዶ የአረሙን መስፋፋት ማቆም ተችሏል፡፡

ለአፍሪካ ተፈጥሯዊ ችግሮች ሳይንሳዊ መፍትሄ ማቅረብ አለብን የሚለው የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ጥምረት ዋና መስሪያ ቤቱ ደቡብ አፍሪካ ሲሆን፤12 ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎችን በአባልነት ይዟል፡፡
ጥምረቱ ከኢትዮጵያ የአዲስ አበባ እና የባህርዳር ዩኒቨርሲቲዎችን በአባልነት ይዟል፡፡
የሺሀሳብ አበራ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3527326
  • Unique Visitors: 199328
  • Published Nodes: 2627
  • Since: 03/23/2016 - 08:03