የአፍሪካ የዱር እንሰሳት ቁጥር በጦርነት ምክንያት እየቀነሰ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ፡፡

ባህርዳር፡ጥር 04 /2010 ዓ/ም(አብመድ)በተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት የሚደረጉ ጦርነቶች ለዝሆኖች፣ጉማሬዎች፣አውራሪሶች እና ሌሎች ትላልቅ አጥቢ እንስሳት ትልቅ ስጋት እየሆኑ መምጣታቸውን በዘርፉ የተደረገ ጥናት ማረጋገጡን አሶሼትድ ፕሬስ ዘገበ ፡፡

ጥናቱን ያካሄዱት ተመራማሪዎች በአፍሪካ ውስጥ እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶች ትላልቅ እንስሳትን ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን ጠቅሰው እ.ኤ.አ. ከ1946 ጀምሮ ከ 70 በመቶ በላይ የሚሆኑ የአፍሪካ የዱር እንስሳት መጠለያዎች ወደጦርነት ቀጣናነት እየተቀየሩ ነው ብለዋል ፡፡

የተለያዩ ዓላማ አንግበው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች የመጀመሪያ ምርጫቸው የዱር እንሰሳቱ ጥብቅ ክልል በመሆኑ የእንሰሳቱ ቁጥር እንዲያሽቆለቁል እያደረገ ነው ይላሉ በአሜሪካ የዬል ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ሕይወት ተመራማሪ ጆውስ ዳስኪን፡፡

ተመራማሪው እንደሚሉት በእነዚህ አመታት ውስጥ በያመቱ 35 በመቶ የሚሆኑ የአጥቢ እንስሳዎች ቁጥር እየቀነሰ ይገኛል ብለዋል አሶሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው፡፡ 

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3693193
  • Unique Visitors: 209289
  • Published Nodes: 2809
  • Since: 03/23/2016 - 08:03