የአጎዋ ጥቅሞችን አፍሪካውያን እየተጠቀሙ አይደለም ሲሉ የቶጎ የንግድ ሚኒስትር ተናገሩ፡፡

ባህር ዳር፡ ነሀሴ 4/2009 ዓ/ም (አብመድ)የቶጎ ንግድ በርናዴቲ ሊግዚም-ባሉኪ  ሚኒስትር እንደሚሉት ዩናይትድ ስቴትስ ለአፍሪካ የሰጠችውን በኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማለትም አፍሪካን ግሮዝ ኦፖርቱኒቲ አክሽን /አገዋ/ የአፍሪካ አገሮች በአግባቡ አልተጠቀሙበትም ብለዋል፡፡

በቶጎ ዋና ከተማ ሎሜ ላይ በተከናወነው 16ተኛው የአጎዋ ውይይት በግል ዘርፉ እና በሲቪክ ማህበራት መካከል በተደረገው ውይይት ላይ የቶጎ  የንግድ ሚኒስትር እና የግል ሴክተሩን ማስተዋወቅ ተጠሪ በርናዴቲ ሊግዚም-ባሉኪ እንዳሉት

በበጀት ዓመቱ በንግዱ አካባቢ እና በአካባቢያዊ አስመጭ እና ላኪዎች መካከል ውህደት ለመፍጠር ያጋጠሙን ችግሮች አጎዋን እንዳንጠቀም እንቅፋት ሆኖብናል ብለዋል፡፡

እንደ ሚኒስትሯ ገለጻ ከሆነ ችግሮችን በማስወገድ በምርት ጥራቷ ተወዳዳሪ የሆነች አፍሪካን መፍጠር እንደሚገባ አትተው በተለይም የአሜሪካን ገበያ ሰብሮ የሚገባ ምርት ማምረት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

በሳብ ሳህራን አፍሪካ ሃገሮች እና በአሜሪካ መካከል ጠንካራ የንግድ ትስስር መፍጠር አስፈላጊ ነውም ብለዋል፡፡

በውይይቱ ላይ ኢኮኖሚያችን በንግዱ ዘርፍ እንዴት እናጠናክር በሚሉ ጉዳዮች ላይ ተመክሯል፡፡

በውይይቱ ላይ ከ38 የሳብ ሰሃራን ሃገሮች የተውጣጡ ከአንድ ሽ በላይ ተሳታፊዎች የተሳተፉ ሲሆን ውይይታቸውን ዛሬ ያጠናቅቃሉ፡፡

ምንጭ፡-ሮይተርስ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3537653
  • Unique Visitors: 199679
  • Published Nodes: 2652
  • Since: 03/23/2016 - 08:03