የአውሮፓ ህብረት የሊቢያ ኤምባሲውን እንደገና ሊከፍት ነው

ባህር ዳር፡ ጥቅምት 1/2010 ዓ/ም (አብመድ)ሊቢያን  ለማረጋጋት ጥረት እያደረገ ላለው የትሪፖሊ መንግስት ፖለቲካዊ ድጋፍ ለመስጠት የተዘጋጀው የአውሮፓ ህብረት የሊቢያ ኤምባሲውን እንደገና ሊከፍት መሆኑን ሮይተርስ ዘገበ ፡፡

እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 19 -20 በብራሰልስ በሚደረገው የአውሮፓ ህብረት መሪዎች ጉባኤ ላይ ህብረቱ በሊቢያ ቋሚ መቀመጫ  ለመክፈት ይፋ መግለጫ ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡

እ.ኤ.አ.በ2011 በሊቢያ በተቀሰቀሰው ግጭት የተነሳ ኤምባሲውን ወደቱኒዚያ ያዛወረው የአውሮፓ ህብረት አሁን በሃገሪቱ እየታየ ያለው መረጋጋት አበረታች በመሆኑ እና የተባበሩት መንግስታት  ለፋዬዝ ሳራጅ መንግስት ዕውቅና በመስጠቱ ህብረቱ በድጋሚ ኤምባሲውን ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ ይገኛል ተብሏል፡፡

 

ከ28 ቱ የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት መካከል የሊቢያ የቀድሞ ቅኝ ገዢ የነበረችው እና የህብረቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆነችው ጣልያን ብቻ ናት ኤምባሲዋን ሳትዘጋ እስካሁን የዘለቀችው ፡፡

የአውሮፓ ህብረት የሳራጅ መንግስት የአፍሪካ ስደተኞችን ፍልሰት ለመቆጣጠርና ወደመጡበት በሰላም ለመመለስ እያደረገ ያለውን ጥረት ከማበረታታት ባለፈ ድጋፍ እየሰጠ መሆኑን አስታውቋል ፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3527321
  • Unique Visitors: 199328
  • Published Nodes: 2627
  • Since: 03/23/2016 - 08:03