የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን በክልሉ ለማስፋፋት የተያዘው እቅድ ተስፋ ሰጭ ውጤቶችን እያሳየ ነው፡-ርዕሰ መስተዳደድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

ባህር ዳር፡ ሰኔ 29 /2009 ዓ/ም (አብመድ)በግል ባለሃብቶች እና የመንግስት ትብብር የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን በክልሉ ለማስፋፋት የተያዘው እቅድ ተስፋ ሰጭ ውጤቶችን እያሳየ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደድርአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተናገሩ፡፡

         ዘርፉን የማንቀሳቀስ አቅም ያላቸውን የግል ባለሃብቶች መንግስት የማስተባበር እና የመደገፍ ኃላፊነቱን ይወጣል ብለዋል፡፡

ከአንድ አመት በፊት ከአራት መቶ በላይ ባለአክሲዮኖችን ይዞ የተቋቋመው የአባይ ኢንዱስትሪያል አክሲዮን ማህበር ክልሉ በተያዘው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መጨረሻ ላይ የሚጠበቀውን ሃገራዊ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ ዕውን ማድረግ የሚቻልበትን ተጨማሪ አቅም ይፈጥርለታል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

     አክሲዮን ማህበሩ እስካሁን ባካሄደው እንቅስቃሴ ኘሮጀክቶችን የማስጠናት፣ ከባለአክሲዮኖች ገንዘብ የመሰብሰብ እና የሚገነቡ ፋብሪካዎችን የመሠረተ ድንጋይ የመጣል ተግባራትን በዋናነት አከናውኗል፡፡ የአባይ ኢንዱስትሪያል አክሲዮን ማህበር እንቅስቃሴ የመንግስት እና የግል ባለሃብቱ አጋርነት ለማምረቻ ኢንዱስትሪው መስፋፋት ወሳኝ መሆኑን ያመላከተ እንደሆነ የአክሲዮን ማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ እና በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የክልሉ ንግድ ኢንዱስትሪ እና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊው አቶ ተስፋዬ ጌታቸው ተናግረዋል፡፡

      አክሲዮን ማህበሩ ከሰሞኑ ባካሄደው የባለአክሲዮኖች አንደኛ አመት መደበኛ እና ድንገተኛ ጉባኤ 4 ቢሊዮን ብር የተፈረመ እና ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ የተከፈለ ካፒታል እንዲሰራ ተገልጿል፡፡

     ዘርፉ ከፍተኛ ካፒታል እና ክህሎት የሚጠይቅ መሆኑ ታውቆ የተቀየሰው የህብረት እንቅስቃሴ በክልሉ ውጤት እየተገኘበት መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ገልፀዋል፡፡

      የአባይ ኢንዱስትሪያል አክሲዮን ማህበር በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ለማቋቋም ካሰባቸው 24 ፋብሪካዎች መካከል የስድስቱን የመሠረት ድንጋይ የመጣል ተግባር ከቅርብ ጊዜ በፊት አከናውኗል፡፡

      የፋብሪካዎቹን ግንባታ ለመጀመር የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራትም እየተከናወኑ ይላሉ የማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ደምስ ተሻገር በአክሲዮን ማህበሩ አንደኛ አመት መደበኛ እና ድንተገኛ ጉባኤ የአክሲዮን ሽያጭ ማፅደቅ እና የአዳዲስ ባለ አክሲዮኖችን የመቀበል የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርትን አዳምጦ የማፅደቅ የአክሲዮን ማህበሩ ኦዲተር ሹመት የማፅደቅ እና ተያያዥ ተግባራትን አከናውኗል፡፡

ቴዎድሮስ ወርቁ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3284013
  • Unique Visitors: 188934
  • Published Nodes: 2588
  • Since: 03/23/2016 - 08:03