የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊእና የዩጋንዳው አቻቸው ዮሪ ሙሶቬኔ የነዳጅ ዘይት ማስተላለፊያ መስመር ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ አስቀመጡ፡፡

 ባህር ዳር፡ ነሀሴ 1/2009 ዓ/ም (አብመድ)የነዳጅ ዘይት ማስተላለፊያ መስመሩ የሚዘረጋው ከኡጋንዳ ሆይማ እስከ ታንዛኒያ የህንድ ውቅያኖስ ወደብ እስከሆነችው የታንጋን ግዛት ነው፡፡

ይህ የምስራቅ አፍሪካ የነዳጅ ዘይት ማስተላለለፊያ  1ሽ 443 ኪ.ሜ. ርቀት እንዲኖረው ተደርጎ የሚገነባ ሲሆን  3.55 ቢሊዮን ዶላር ወጭ ይደረግበታልም ነው የተባለው ፡፡ ፕሮጀክቱ ሥራውን ሲጀምር በቀን እስከ 200 ሺህ ሊትር ነዳጅ ማጓጓዝ ይችላል፡፡

ይህ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ በዓለም ላይ ረዥሙ በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰራ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ይሆናልም ነው የተባለው፡፡

ባለስልጣናቱ  በ2018 መጀመሪያ ላይ እንደሚጀምርና የ36 ወራት የግንባታ ጊዜ እንደተሰጠው አብራርተዋል፡፡ የሁለቱ ሃገራ መሪዎች የመሰረት ዲንጋይ ያስቀመጡት ትልቅ ፕሮጀክት፣ ከ 6ሺህ እስከ 10ሺህ የሚደርሱ የሥራ ዕድሎችን እንደሚፈጥር ይጠበቃል፡፡

የኡጋንዳ የነዳጅ ዘይት ኩባንያዎች አሁን አምርተው ከሚያጠራቅሙት  1.7 ቢሊዮን  በርሜል  በዓመት ወደ 6.5 ቢሊዮን በርሜል ማሳደግ ያስችላቸዋል፡፡

ምንጭ፡-አሶሸትድ ፕሬስ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3527365
  • Unique Visitors: 199329
  • Published Nodes: 2627
  • Since: 03/23/2016 - 08:03