የቦትስዋናው አትሌት አይዛክ ማካዋላ በምግብ መመረዝ ከውድድር ውጭ ሆነ

ባህር ዳር፡ ነሀሴ 2/2009 ዓ/ም (አብመድ)የቦትስዋናው አትሌት አይዛክ ማካዋበምግብ መመረዝ ምክንያት ለንደን በሚካሄደው የ200 ሜትር የአትሌቲክስ ወድድር ውጭ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በዓለም አቀፍ ውድድሮች በምግብ መመረዝ ምክንያት ከውድድር ውጭ የሆነ አትሌት ብዙም አጋጥሞ እንደማያውቅ ያተተው የሮይተርስ ዘገባ ሰኞ እለት የቦትስዋናው አትሌት አይዛክ ማካዋ በምግብ መመረዝ ምክንያት ለንደን በሚካሄደው የ200 ሜትር የአትሌቲክስ ወድድር እንደማይካፈል በአትሌቱ የፌስ ቡክ ገጽ አማካኝነት አስታውቋል ብሏል፡፡

አዘጋጆቹ አትሌቱ ይህን ከማስታወቁ አስቀድሞ በሆቴሉ ላይ መግለጫ የሰጠ ሲሆን በመግለጫው እንዳለው በርከት ያሉ ቡድኖች በሆቴሉ ውስጥ የጋስትሮንትሪቲስ በሽታ ተከስቶ በአትሌቶች ላይ ጉዳት እያደረሰ እንደሆነ ሪፖርት እንዳደረጉ ይፋ  አድርገዋል፡፡

 እንደ አዘጋጅ ኮሚቴው መግለጫ ከሆነ የተጎዱ አትሌቶችን በቡድኑ የህክምና ቡድን እና በለንደን ኦሎምፒክ ኮሚቴ የሕክምና ባልደረቦች ድጋፍ እየተደረገላቸው  ነው ፡፡ በተጨማሪም ክስተቱን ለመቆጣጠርና ለመያዝ ከህዝብ ጤና ጥበቃ ድርጅት ጋር እየሰራን ነው ብሏል፡፡

የዓለማቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በመግለጫው እንዳለው ጉዳዩ  ከውድድር ውጭ የሚያደርግ አልነበረም፡፡ ይሁን እንጅ ከሆቴሎች ጋር በተገናኘ በፌስቡክ ገጹ እንደዚህ አይነት መልዕክቶችን ማስተላለፍ ሌሎች አትሌቶች ላይ ጫና የሚፈጥር ነው በሚል ጉዳዩን ኮንኗል፡፡

ምንጭ፡-ሮይተርስ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3537660
  • Unique Visitors: 199679
  • Published Nodes: 2652
  • Since: 03/23/2016 - 08:03