የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ባይሌ ዳምጤ አዲስ ለተሾሙት ለዶከተር ፍሬው ተገኘ ስልጣናቸውን በይፋ አስረከቡ፡፡

ባህርዳር፡ጥር 01 /2010 ዓ/ም(አብመድ)ያለፉትን 7 ዓመታት ዩኒቨርሲቲውን የመሩት ዶከተር ባይሌ ዳምጤ ከጎናቸው ለነበሩ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ እንደዚህ ዓይነቱ ግልፅ የሆነ የስራ ርክክብ ተቋማዊ ባህል ሆኖ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ 
በፕሬዘዳንታዊ ምርጫው የዩኒቨርሲቲው ማህበረስብ ለነበረው ተሳትፎም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ዶ/ር ፍሬው ተገኝ ነገ ጥር 1 ቀን 2010 ዓ.ም በይፋ ስራቸውን ጀምረዋል፡፡
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ለዶክተር ባይሌ ዳምጤ ሽልማት አበርክቷል፡፡
ምንጭ፡-ባህር ዳር ዪኒቨርሲቲ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3050313
  • Unique Visitors: 184002
  • Published Nodes: 2537
  • Since: 03/23/2016 - 08:03