የቀድሞው የአርሰናል አማካይ ቶማስ ሮዝስኪ ራሱን ከእግር ኳስ አገለለ፡፡

ባህርዳር ፡ታህሳስ 12/2010 ዓ/ም(አብመድ)በ2006 ከቦርሲያ ዶርቱመንድ መድፈኞቹን ከተቀላቀለ በኋላ በ10 ዓመታት በአርሰናል ቆይታው 2 የFA ዋንጫዎችን ማንሳት ችሏል፡፡Image result for rosicky stops football

      በሃገሩ ቸክ ሪፐብሊክ ስፖርታ ኘራግ ክለብ እየተጫወተ የነበረው ሮዝስኪ ፤ጉዳት በዚህ ሰዓት እግር ኳስ ለማቆሜ ዋናው ምክንያት ነው ብሏል፡፡

       በአሁኑ ሰዓት ኘሮፌሽናል እግር ኳስ በሚፈልገው ደረጃ ሰውነቴ ዝግጁ አይደለም፡፡ ክለቤን ከዚህ በላይ ባለማገልገሌ አዝናለሁ ብሏል ሮዝስኪ በስፓርታ ኘራግ ይፋዊ ድረገፅ፡፡

       የ37 ዓመቱ ሮዝስኪ ከቦርሲያ ዶርቱመንድ፣ አርሰናልና ስፖርታ ኘራግ በተጨማሪ ለሀገሩ ቸክ 105 ጊዜ በመሰለፍ በ5 ታላላቅ ውድድሮች ላይ ተሳትፏል፡፡

     በአርሰናል ደግሞ 246 ጊዜ ተሰልፎ 28 ግቦችን አስቆጥሯል፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3870115
  • Unique Visitors: 214834
  • Published Nodes: 2859
  • Since: 03/23/2016 - 08:03