የሞሮኮ መሐንዲሶች በአፍሪካ ፈጣን ባቡር ለመሞከር እየተዘጋጁ ነው፡፡

ባህር ዳር፡ ጥቅምት 1/2010 ዓ/ም (አብመድ)የሞሮኮ  መሐንዲሶች በሰዓት 320 ኪሎ ሜትር መጓዝ የሚችል ፈጣን ባቡር  በዚህ  ሳምንት ውስጥ  ለመሞከር  እየሰሩ መሆናቸውን  አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል ፡፡

በሰሜናዊ ሞሮኮ ከኬኒትራ - ታንጀርስ ከተሞች መካከል የተሞከረው ፈጣን ባቡር በሰዓት 275 ኪሎ ሜትር መጓዝ መቻሉን የባቡር አገልግሎቱን የሚያስተባብረው ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዣን ኢቬስ  ሌ ድሪያን እንደሚሉት በፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ እና በሞሮኮ መንግስት  መካከል የባቡር ትራንስፖርትን ለማስፋፋት የሚያስችል የብድር ውል መፈረሙን ተናግረው "የባቡር  አገልግሎቱ  የፈረንሳይ-ሞሮኮ የሁለትዮሽ ግንኙነት  መገለጫ ነው" ብለዋል::

አዲስ የሚጀመረው የባቡር አገልግሎት  የሞሮኮ ከተሞች በሆኑት ካዛብላንካ እና ታንጀርስ መካከል ያለውን ጉዞ የሚያቀላጥፍ ከመሆኑ በተጨማሪ በሰሜን አፍሪካ  ቀጣና ውስጥ ያለውን የየብስ ጉዞ ከሁለት ሰዓት በላይ ስለሚያሳጥረው  የሃገራቱን  የኢኮኖሚ እድገት በሁለት  ሦስተኛ  ያሳድገዋል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡

የዚህ ፈጣን ባቡር ፕሮጀክት  ወጪ ከፈረንሣይ መንግስት  በተገኘ 50 በመቶ ብድር  የተሸፈነ ሲሆን የገንዘብ መጠኑም  2.4 ቢሊዮን  የአሜሪካ ዶላር  እንደሚደርስ ታውቋል፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3884829
  • Unique Visitors: 215544
  • Published Nodes: 2870
  • Since: 03/23/2016 - 08:03