የምእራብ አፍሪካ የኢኮኖሚክ ማህበረሰብ ( ኢኮዋስ ) አካባቢውን ከበሽታ ለመከላከል በማሰብ ማዕከል ማቋቋሙን አስታውቋል፡፡

ባህር ዳር፡ ሰኔ 12 /2009 ዓ/ም (አብመድ)የምእራብ አፍሪካ የኢኮኖሚክ ማህበረሰብ  ኢኮዋስ አባል ሃገራት በቀጣናው በሽታዎችን ለመቆጣጠር የሚያስችል ማዕከል  ለማቋቋም በቀረበው ሃሳብ ላይ ከተወያዩ በኋላ ተቀባይነትን ማግኘቱን  ሲ ጂ ቲ ኤን አስታውቋል ፡፡

ማዕከሉ ወረርሽኝን  በመዋጋት ረገድ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት አባል ሃገራቱ  የእንስሳት እና  የአካባቢ ጤናን  በመጠበቅ በኩል ከፍተኛ ሚና ያጫወታል ተብሏል ፡፡

የኢኮዋስ ምክትል ፕሬዝዳንት ኤድዋርድ ሲንጋቲ እንዳሉት አባል ሃገራቱ  እንደኢቦላ  እና ፖሊዮ የመሳሰሉ አጣዳፊ እና ጊዜ የማይሰጡ  ወረርሽኞች በሚከሰቱበት ጊዜ ቀሪው አለም እስኪደርስ ድረስ የሚከሰተውን ችግር ለመፍታት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

ምንጭ፡-ሲ  ጂ ቲ ኤን

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3284035
  • Unique Visitors: 188935
  • Published Nodes: 2588
  • Since: 03/23/2016 - 08:03