የምስራቅ አፍሪካ የንግድ እንቅስቃሴን ለማሳደግ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የፍጥነት መንገድ ለመስራት ኬንያ በእንቅስቃሴ ላይ መሆኗን አስታወቀች፡፡

ባህር ዳር፡ ነሀሴ 1/2009 ዓ/ም (አብመድ)ኬንያ በምስራቅ አፍሪካ የንግድ ልውውጥ ለማሳደግ የከፍተኛ ፍጥነት አውራ ጎዳና ለመገንባት አቅዳ እየተንቀሳቀሰች ነው፡፡

የኬንያ ብሔራዊ የከፍተኛ ፍጥነት መንገዶች ባለሥልጣን  ዋና ዳይሬክተር ፒተር ሙንዲኒያ እንዳሉት አሁን የሚገነባው 473 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው የፍጥነት መንገድ ከምስራቅ አፍሪካ ሃራት ጋር ያለውን የንግድ ትስስር የበለጠ ለማሳደግ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል፡፡መንገዱ በናይሮቢ እና በሞምባሳ ወደብ መካከል ያለውን ትራንስፖርት ቀልጣፋ ለማድረግ ትልቅ እገዛ ያደርጋል፡፡

መንገዱ በኬንያ ብሔራዊ የትራንስፖርት ስርዓት እንደ ማዕከላዊ ስፍራ ሆኖ ያገለግላል የሚለው ባለስልጣኑ ከኬንያ በተጨማሪ በኡጋንዳ ፣ሩዋንዳ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውስጥ ንግድ እና ልማት እንዲስፋፋ ማድረግ ያስችላል፡፡

መንገዱ በሚቀጥሉት ስድስት ዓመታት ውስጥ በአሥር ክፍሎች ይጠናቀቃል፡፡

ዋና ዳይሬክተር ፒተር ሙንዲኒያ እንደገለጹት የፕሮጀክቱ ዲዛይን ቀድሞ ማለቁን ተናግረው በሰዓት በ120 ኪሎ ሜትር መጓዝ እንዲያስችል ተደርጎ ይገነባል ይህም ከናይሮቢ ተነስቶ ሞምባሳ ለመድረስ ከዚህ በፊት አስር ሰዓት ይፈጅ የነበረ ሲሆን አሁን በሚገነባው የፍጥነት መንገድ  ወደ አራት ሰዓት ጉዞ ይቀንሳል፡፡ ይህም ወደ ውጭ ለሚላኩ እቃዎች እና ወደሃገር ውስጥ ለሚገቡ እቀዎች በጊዜ መድረስ እና የተሻለ የንግድ እንቅስቃሴ እንዲኖር ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተር ፒተር ሙንዲኒያ አክለውም በአሁኑ ጊዜ ከ 90 ከመቶ በላይ የሚሆነው የሃገሪቱ ከውጭ የሚገባው ሸቀጥ በመንገድ ትራንስፖርት የሚጓጓዝ ሲሆን በመንገድ ትራንስፖርት መጓተት ምክንያት ለመዘግየት የሚገደዱትን የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ችግር ይፈታል፡፡ ለረጅም ጊዜ የንግድ እና የኢንዱስትሪ ዕድገት መሠረት ይሆናል ብለዋል፡፡

ምንጭ፡-ሲጂቲኤን

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3537658
  • Unique Visitors: 199679
  • Published Nodes: 2652
  • Since: 03/23/2016 - 08:03