የመንግስት ፋይናንስ ድርጅቶች ጠቅላላ ሀብት መጠን 523 ቢሊዮን ብር መድረሱን የመንግስት ፋይናንስ ድርጅቶች ኤጀንሲ አስታወቀ።

ባህር ዳር፡ ነሀሴ 2/2009 ዓ/ም (አብመድ)የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ስንታየው ወልደሚካኤል እንደገለፁት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣የኢትዮጵያ ልማት ባንክና የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ጠቅላላ ሀብት ከግማሽ ትሪሊዮን ብር በላይ ሆኗል።

ድርጅቶቹ በ2009 ዓ.ም በጀት አመት ጠቅላላ ሀብታቸውን 517 ቢሊዮን ብር ለማድረስ እቅድ የነበራቸው ሲሆን የሐብት ክምችታቸውን 523 ቢሊዮን ብር አድርሰውታል።

ይህም ባለፈው አመት ከነበራቸው ጠቅላላ ሀብት ጋር ሲነፃፀር የ82 ነጥብ 64 ቢሊዮን ብር ጭማሪ አለው ያሉት ዳይሬክተሩ ከጠቅላላ ሐብታቸው ውስጥ 332 ነጥብ 12 ቢሊዮን ብሩ የተጣራ የገንዘብ ሃብት መሆኑን ገልፀዋል።

ከውጭ ምንዛሬ ገቢ፣ከሃዋላ፣ከብድር የሚገኝ ገቢና ሌሎች የገቢ አይነቶች ለተቋማቱ ገቢ መጨመር ዋነኛ ምክንያቶች መሆናቸው ተጠቅሷል።

ከሶስቱ የፋይናስ ተቋማት ጠቅላላው ሀብት ውስጥም 85 በመቶ የሚሆነውን ወይም 465 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድርሻ እንደሆነም ተናግረዋል።

በተጨማሪም 53 ነጥብ 12 ቢሊዮን ብሩ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፣ ቀሪው 4 ነጥብ 12 ቢሊዮን ብር ደግሞ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት መሆኑን ገልፀዋል።

ድርጅቶቹ በ2009 በጀት አመት 15 ነጥብ 64 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ያገኙ ሲሆን ከትርፉ 14 ነጥብ 62 ቢሊዮን ብሩ ወይም 95 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሆኑን ዶክተር ስንታየሁ ገልፀዋል።

ena

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3284032
  • Unique Visitors: 188935
  • Published Nodes: 2588
  • Since: 03/23/2016 - 08:03