የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በ10 ነጥብ 9 በመቶ አድጓል፡-የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ

ባህር ዳር፡ መስከረም 29/2010 ዓ/ም (አብመድ)ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሶስተኛ የስራ ዘመን የመክፈቻ ንግግር ላይ እንዳሉት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ 10 ነጥብ 9 በመቶ እድገት ማስመዝገቡን ገልጸዋል፡፡

Image may contain: 1 person, suit
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ አክለውም ከታቀደው አንጻር ኢኮኖሚው ማገገሙን ያሳያል ብለዋል፡፡


በንጽጽር እንደገለጹትም ግብርና 6 ነጥብ 7 በመቶ ፣የኢንዱስትሪ ዘርፍ የ18 ነጥብ 7 በመቶ እና የአገልግሎት ዘርፍ 10 ነጥብ 3 በመቶ ድርሻ እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡


የኢኮኖሚው እድገት በሚቀጥለው ዓመትም 11 ነጥብ 1 በመቶ እንዲሆን መታቀዱን ገልጸዋል፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3527328
  • Unique Visitors: 199328
  • Published Nodes: 2627
  • Since: 03/23/2016 - 08:03