ዛምቢያ መስኖ በስፋት መጠቀሟ የምግብ እጥረቷን ለማሟላት እንደረዳት መንግስት ገለጸ፡፡

ባህር ዳር፡ መስከረም 30/2010 ዓ/ም (አብመድ)ከሰሃራ በታች ባሉ አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገራት ከሁለት አስርት አመታት በፊት የጀመረው ድርቅ በዛምቢያም የምግብ እጥረት ሲያስከትል መቆየቱን መንግስት ገልጾ አሁን ግን የመስኖ ልማት በመጀመር ክፍተቱን ለመሸፈን መቻሉን አስታውቋል ፡፡

 

እንደ ዛምቢያ መንግስት ማብራሪያ ከሆነ በድርቅ ምክንያት የሚፈጠረውን የምግብ ክፍተት ለመሙላት በሃገር አቀፍ ደረጃ መስኖን በስፋት የመጠቀም ዝንባሌ በመስፋፋቱ የሃገሪቱ አርሶ አደሮች የነበራቸውን አስተሳሰብ ቀይረው ከፍተኛ ውጤት እንዳስመዘገቡ ቢቢሲ ዘግቧል ፡፡

የተፈጠረውን የከፋ የውኃ እጥረት ለመቋቋም አርሶ አደሮቹ የመስኖ ቴክኖሎጂን እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው በተሰጣቸው ስልጠና መሠረት ከዚህ በፊት ይፈጠር የነበረው የዝናብ መቆራረጥ ብዙም ሳይሰማቸው በዓመት እስከ ሶስት ጊዜ የማምረት እድል እንደፈጠረላቸው ይናገራሉ፡፡

በዚህም መሠረት ዛምቢያ የምግብ ፍጆታዋን ከማሟላት በተጨማሪ ምግብ እስከማከማቸት መድረሷን መንግስት እንደገለጸ ሺንዋ ዘግቧል

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3433619
  • Unique Visitors: 194892
  • Published Nodes: 2605
  • Since: 03/23/2016 - 08:03