እስራኤል 40 ሺ አፍሪቃውያን ስደተኞችን ያለፍላጎታቸው ከሃገሯ ልታስወጣ ነው

ባህር ዳር: ህዳር 11/2010(አብመድ) እስራኤል 40 ሺ አፍሪካዊ ስደተኞችን ከአገር ለማስወጣት ማቀዷን የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ሲያስታውቁ ካቢኔውም የስደተኞችን ማዕከል ለመዝጋት ድምጽ ሰጥቷል፡፡Image may contain: one or more people, people standing and outdoor
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቢኔ ባወጣው መግለጫ ጥገኝነት ጠያቂዎቹ የሦስት ወር የጊዜ ገደብ ተሰጥቷቸው ከሃገር እንዲወጡ ውሳኔ ሲያስተላልፍ በደቡባዊ እስራኤል የሚገኙት የስደተኞች ማቆያ ማእከላትም እንዲዘጉ ስምምነት ላይ መደረሱን አስታውቋል ፡፡ 
አብዛኛዎቹ አፍሪካውያን ስደተኞች ያለ በቂ ምክንያት በሰዎች ግፊት ተታለው የሚመጡ ከመሆናቸው በቀር አመዛኙን ቁጥር የያዙት እውነተኛ ስደተኞች ሳይሆኑ ወንጀለኞች በመሆናቸው ሃገራችንን መልቀቅ ይኖርባቸዋል ሲል የእስራኤል መንግስት ፈርጇቸዋል፡፡
የሃገሪቱ የሕዝብ ደህንነት ሚኒስቴር በበኩሉ በስደተኝነት ስም ወደሃገራችን ከገቡት መካከል በርካቶቹ በስደተኞች ስም የሚነግዱ አጭበርባሪዎች ስለሆኑ አገሪቱን የመልቀቅ አሊያም የመታሰር ምርጫ ይኖራቸዋል የሚል አስተያየት ሰጥቷል ፡፡ 
እስራኤል አሁን ከሃገር ለማስወጣት የዛተችባቸውን የአፍሪካ ስደተኞች ወደ አገራቸው ትመልሳቸው ወይም ወደሶስተኛ ሀገር ትላካቸው ለጊዜው ግልጽ አለመሆኑን መረጃው አመልክቷል ፡፡ 
ይሁን እንጂ እስራኤል ውስጥ የሚገኙ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ድርጊቱን በመቃወም "እስራኤል ስደተኞቿን ከሃገር ከማስወጣት ይልቅ ሌሎች ሀገራት ጥገኝነት ጠያቂዎችን እንደሚንከባከቡት ሁሉ መጠበቅ እና ማስተናገድ ይገባታል ››ማለታቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል ፡፡ 
ጥገኝነት ፈላጊዎቹ በተለይም የሱዳን እና የኤርትራ ዜጎች ሲሆኑ እ ኤ አ ከ2000 ቀደም ብሎ የግብጽን ሲናይ በረሃ አቋርጠው ወደእስራኤል የገቡ ናቸው ፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3693162
  • Unique Visitors: 209288
  • Published Nodes: 2809
  • Since: 03/23/2016 - 08:03