ኢትዮ ቴሌኮም በጎንደር ከተማ ‹‹ሪጅን›› ባለማቋቋሙ ተገቢውን አገልግሎት እያገኘን አይደለም ፡- የጎንደር ከተማና በዙሪያው የሚገኙ ደንበኞች

ባህር ዳር: ህዳር 12/2010(አብመድ)ደንበኞቹ ይህን ያሉት የኢትዮ -ቴሌኮም ሰሜን ምዕራብ ሪጅን በጎንደር ከተማ ከህዝብ ክንፍ ጋር ባደረገው ውይይት ወቅት ነው።

ኢትዮ ቴሌኮም እየሰጠ ባለው አገልግሎት የኔትወርክ ጥራቱ ደካማ በመሆኑም ለሞባይል ግንኙነትና ለፋይናንስ ተቋማት አገልግሎት እንቅፋት እየፈጠረ ነው ብለዋል ደንበኞቹ።

የሰሜን ጎንደር ዞን ከ5 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚኖርበትና በርካታ ደንበኞች ያሉበት ሆኖ ሳለ በጎንደር ከተማ ማዕከል(ሪጅን) ስላልተቋቋመለት ደንበኞቹ ከኢትዮ -ቴሌኮም ተገቢውን ማህበራዊ አገልግሎት እየሰጠ አይደለም ብለዋል።

ይህ ጥያቄያችን ለረጅም አመታት ቢቀርብም ምላሽ ባለማግኘታችን ከዋና ማዕከሉ ያሉ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች መጥተው ሊያወያዩን ይገባል ብለዋል ተሳታፊዎቹ።

የኔትወርክ ዝርጋታ ሲያከናውንም ከሌሎች ተቋማት ጋር ባለመናበቡ የከተማዋን መሰረተ ልማት እያበላሸ ነው ሲሉ ደንበኞቹ ቅሬታ አቅርበዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ሰሜን ምዕራብ ሪጅን ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ ይመር ተፈራ ደንበኞቹ ያነሱትን የአገልግሎት አሰጣጥ ቅሬታ ለመፍታት እንሰራለን ብለዋል።

ኢትዮ -ቴሌኮም በጎንደር ከተማ ሪጅን ማቋቋም እንዳለበት እናምናለን ያሉት አቶ ይመር ተግባራዊ እንዲሆን የከፍተኛ አመራሩን ውሳኔን ይጠይቃል ብለዋል።

የሪጅኑ ተቋም እንዲገነባና ስራ እንዲጀምርም እየተነጋገርን ነው ፤ዛሬ ላይ የተነሳውን የደንበኞች ጥያቄ ለማስመለስ በቅርብ ጊዜ ከከፍተኛ አመራሮች ጋር የህዝብ መድረክ እንፈጥራለን ብለዋል።

ስማቸው እሸቴ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3693161
  • Unique Visitors: 209288
  • Published Nodes: 2809
  • Since: 03/23/2016 - 08:03