ኢትዮጵያና ሱዳን በቀጠናው ከደህንነት ጋር የተያያዙ ችግሮችን በጋራ ለመመከት ተስማምተዋል፡፡

ስምምነቱ የሱዳን የመከላከያ ሚኒስትሩ በሁለቱ ሀገራት አዋሳኝ አካባቢዎቸች ካለው የደህንነት ጉዳይ ጋር በተያያዘ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ለመምከር በአዲስ አበባ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው፡፡Image may contain: 3 people, people smiling, people standing and suit

የሱዳን መከላከያ ሚኒስትሩ ኢማድ አልዲን አዋዲን አንደ ሀገር የሚገጥማት ማንኛውም ተግዳሮት የሁለቱም ሀገራት የጋራ ችግር መሆኑን ገልጸው ማንኛውንም አይነት ችግር ለመመከት የጋራ ጥረት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይላማርያም ደሳለኝ ሀገራቸው ብሔራዊ ፍላጎቷን የሚጻረሩ ጉዳዮችን ለመከላከል ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸው በኢትዮጵያና ሱዳን መካከል ለዘመናት የዘለቀው ስትራቴጂያዊ አጋርነትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ከምንጊዜውም በላይ ወደከፍተኛ ደረጃ መሸጋገሩን የቻይናው ዓለም አቀፍ ቴሌቪዥን ኔትዎርክ ሪፖርቶችን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
ኢዜአ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3433497
  • Unique Visitors: 194890
  • Published Nodes: 2605
  • Since: 03/23/2016 - 08:03