አንጋፋው አርቲስት ሀብተሚካኤል ደምሴ በመኪና አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡

ባህር ዳር፡ መስከረም 29/2010 ዓ/ም (አብመድ)አንጋፋው የባህል ሙዚቃ ተጫዋች አርቲስት ሀብተሚካኤል ደምሴ ዛሬ መስከረም 29 ቀን ከጥዋቱ 4 ሰዓት ላይ አበበ ቢቂላ ስታዲየም አካባቢ መኪናውን አቁሞ መንገድ እየተሻገረ ሳለ አውቶብስ ገጭቶት ህይወቱ አለፈ ፡፡

Image may contain: 4 people, people smiling, people standing

አደጋው በደረሰበት ሰዓት በአካባቢው የነበሩ ሲቪሎችና ፖሊሶች ህይወቱን ለማትረፍ ፈጥነው ከዮሐንስ ቤተክርስቲያን ጀርባ ወደሚገኘው አቤት ሆስፒታል ይዘውት ቢሄዱም አደጋው የከፋ በመሆኑ መርዳት አለመቻሉ ታውቋል ፡፡

 

ለቤተሰቦችና አድናቂዎች ድርጅቱ መጽናናትን ይመኛል ፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3527327
  • Unique Visitors: 199328
  • Published Nodes: 2627
  • Since: 03/23/2016 - 08:03