አስቸኳይ እና የማይቋረጡ ጉዳዮች በመደበኛና በተረኛ ችሎቶች አገልግሎት በክረምቱ ይሰጣል፡-የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት

ባህር ዳር፡ ነሀሴ 10/2009 ዓ/ም (አብመድ)የፌደራል ፍርድ ቤቶች በክረምት ወራት በከፊል የሚዘጉ ቢሆንም መሰረታዊ የህዝብና የዜጐች መብቶች የሚነኩ አስቸኳይ እና የማይቋረጡ ጉዳዮች በመደበኛና በተረኛ ችሎቶች አገልግሎት መስጠት እንደሚቀጥሉ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

          ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ከፍተኛና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለከተው ሶስቱ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከነሐሴ እስከ መስከረም በከፊል ዝግ ቢሆኑም መደበኛ ክርክር እስኪጀምር ይጠበቅ ቢባል በሃገር ሰላምና ፀጥታ፣ በዜጐችና ተከራካሪ ወገኖች መሰረታዊ መብቶች ላይ ከባድ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ጉዳዮች በመደበኛ እና በተረኛ ችሎቶች የዳኝነት አገልግሎት ይቀጥላል፡፡

          ያለምንም እረፍት ቅዳሜና እሁድ ጭምር መዝገብ በመመርመር ከባዱን የዳኝነት ስራ ይቀጥላል ሲል የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባደረሰን መረጃ አመላክቷል፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3300944
  • Unique Visitors: 189354
  • Published Nodes: 2588
  • Since: 03/23/2016 - 08:03