አምስት ክልሎችና አዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በ2010 በጀት ዓመት ለወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ የተመደበውን ተዘዋዋሪ ብድር እንዳልወሰዱ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር አስታወቀ።

 

ባህርዳር፡ጥር የካቲት 1 /2010 ዓ/ም(አብመድ)አምስቱ ክልሎች ትግራይ፣ አማራ፣ ሃረሪ፣ ፣ አፋርና ጋምቤላ ናቸው።
ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም ተከስተ የጸደቀውን የወጣቶች ተዘዋዋሪ በጀት ማቅረብና ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ማከፋፈል የመስሪያ ቤታቸው ኃላፊነት ቢሆንም አምስቱ ክልሎችና አዲስ አበባ መስተዳድር የተፈቀደላቸውን በጀት ለመጠቀም ምንም አይነት ጥያቄ እንዳላቀረቡ ነው ያብራሩት።

ክልሎቹ የተፈቀደላቸውን በጀት ያልተጠቀሙበትን ምክንያት ለማወቅ በሚመለከተው አካል የማጣራት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
ክልሎቹ የተመደበላቸውን በጀት ጥቅም ላይ በማዋል የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መረባረብ እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

የፌደራሉ መንግስት በ2010 ዓ.ም ለወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ አምስት ቢሊዮን ብር መመደቡ ይታወሳል፡፡

ከዚህ ውስጥም በግማሽ ዓመቱ ክልሎቹ የወሰዱት 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ያህሉን ብቻ መሆኑን ሚንስትሩ ገልጸው በአፈጻጸም ደረጃ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን አንስተዋል።

ክልሎቹ የተመደበላቸውን በጀት አለመውሰዳቸው የመንግሥትን የስራ እድል ፈጠራ ስራ አፈጻጸም ዝቅተኛ እንዳደረገውም ተናግረዋል፡፡
ena

 

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3870108
  • Unique Visitors: 214834
  • Published Nodes: 2859
  • Since: 03/23/2016 - 08:03