አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር በኢኮኖሚው ዘርፍ በጋራ ትሰራለች፡-በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ

ባህር ዳር፡ ጥቅምት 1/2010 ዓ/ም (አብመድ)የአሜሪካው አምባሳደር ማይክል ራይነር ዛሬ በአማራ ክልል ጉብኝት አድርገዋል፡፡በጉብኝታቸውም በክልሉ ከሚገኙት ከባህር ዳር እና ጎንደር ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጋራ ለመስራት ውይይት አድርገዋል፡፡Image may contain: one or more people and people sitting

አምባሳደሩ እንዳሉትም ሀገራቸው አሜሪካ በትምህርት ዘርፍ-በሳይንስና ቴክኖሎጂ ፣በሲቪክ ማህበራት ፣በስራ ፈጠራ፣በስራ አመራር እና በሰብአዊ ልማት ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ እንደምትሰራ ገልጸዋል፡፡
በተለይም ሀገራቸው አሜሪካ በወጣቶች ዙሪያ ስራዎችን ትሰራለች፤ በቀጣይም አጠናክራ ትቀጥላለች ፡፡

ሁለቱ ሀገራት የቆየ ጠንካራ ወዳጅነት ያላቸው በመሆናቸው አሁንም በትራምፕ አስተዳደር የመንግስት ለመንግስት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ከመቸውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል አምባሳደሩ፡፡No automatic alt text available.

ስለ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት ሀሳብ የሰጡት አምባሳደር ራይነር ‹‹ኢትዮጵያ በፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ላይ ትገኛለች፡፡ኢኮኖሚው ተጠናክሮ እንዲቀጥልም የሀገራቸው አሜሪካ ሁለንተናዊ ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል›› ብለዋል፡፡
የጣና ሀይቅ ገዳማትን የጎበኙት አምባሳደሩ‹‹ ሀገሪቱ የበርካታ መስህብ ሀብቶች ባለጸጋ ነች፡፡የጎበኘኋቸው የጣና ገዳማትም እጅጉን አስደንቀውኛል›› ብለዋል፡፡

የአሜሪካ መንግስት ድጋፍ በሚያደርግለት ገነሜ የህዝብ ቤተመጽሀፍት አምባሳደሩ ተገኝተው የ35ኛውን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆን ፊትዝጀራልድ ኬኔዲ መቶኛ ዓመት መታሰቢያን ዘክረዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ፣ለሰዎች እኩልነት እና ፍትሀዊ ዓለም እንድትኖረን ቀድመው ይሰብኩ የነበሩ መሪ መሆናቸውንና ለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መጠናከር ከፍተኛ ሚና መጫወታቸውን የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ባይሌ ዳምጤ ተናግረዋል፡፡Image may contain: 1 person, smiling, stripes

ፕሬዝዳንቱ አክለውም ኬኔዲ ሰዎች ወደ ጨረቃ እንዲጓዙ እና እንዲመራመሩ ትልቁን ሚና የወሰዱት ፕሬዝዳንት ናቸው፡፡ይህንንም ያደረጉት አዲስ ነገር መስራት ስለሚወዱ እና በፈተና ውስጥ ማሸነፍ እንደሚቻል ስለሚያውቁ ነው፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያም ከአሜሪካ ብዙ ነገር ልትማር ትችላለች፡፡ የበርካታ ብሄሮችና ብሄረሰቦች መገኛ የሆነችው ኢትዮጵያ፤ ህብረ ብሄራዊ ከሆነችው አሜሪካ እንዴት ተዋዶና ለሀገር አንድ ሆኖ መቆም እንደሚገባ ልንማር ይገባል ብለዋል፡፡Image may contain: 6 people, people smiling, people sitting, suit and indoor

አምባሳደር ማይክል ራይነር ተሹመው ወደ ኢትዮጵያ በመጡ በ10ኛ ቀናቸው በአማራ ክልል ያደረጉት የመጀመሪያው ጉብኝታቸው ነው፡፡
በመሠረት አስማረ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3527319
  • Unique Visitors: 199328
  • Published Nodes: 2627
  • Since: 03/23/2016 - 08:03