አልጄሪያ ከውጭ የምታስገባቸውን የሞባይል ስልኮች፣የቤት እቃዎች እና የምግብ እቃዎችን አገደች፡፡

ባህርዳር፡ጥር 03 /2010 ዓ/ም(አብመድ)አልጀሪያ የወጪ እና ገቢ ንግዷን ለመቆጣጠር ተንቀሳቃሽ ስልኮችን፣የቤት እቃዎችን እንዲሁም የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶችን ጨምሮ ሌሎች 900 ያህል ሸቀጦችን ከውጭ እንዳይገቡ ማገዷን ሮይተርስ ዘገበ፡፡

እገዳው ተግባራዊ የሚደረገው በቤት እቃዎች፣በአትክልት እና ፍራፍሬ፣በቸኮሌት ምርት፣በዱቄት፣ በፓስታ፣ በጭማቂ፣በታሸገ ውኃ እና በአንዳንድ የግንባታ ቁሳቁሶች ላይ ይሆናል፡፡

እነዚህን ምርቶች የማስመጣት ሂደት በጊዜ የተገደበ ሲሆን ቀስ በቀስ እገዳው እንዲነሳ ማድረግ ወይም ግብር በመጨመር እገዳው እንዲነሳ ይደረጋል ብሏል መንግስት በመግለጫው፡፡

በእገዳው የአልጄሪያ መንግስት 30 ቢሊዮን ዶላር ከውጭ ምንዛሬ የሚያስቀር ሲሆን ባለፈው የፈረንጆች አመት ሃገሪቱ ለእነዚህ እቃዎች 45 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ሲያደርግ በ2016 ደግሞ 46.7 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማውጣቱ ታውቋል ፡፡

በዚህም መሠረት ይህ እገዳ የተጋነነውን ምንዛሬ በማስቀረት የወጭ እና ገቢ ንግዱን እንዲጣጣም ያደርጋል ብሏል መንግስት በመግለጫው፡፡

አልጄሪያ 60 በመቶ የሚሆነው የበጀት ምንጯ የተመሰረተው በነዳጅ እና ጋዝ ላይ ቢሆንም በዋጋው መውደቅ ምክንያት ገቢዋ መቀዛቀዙን ዘገባው አስረድቷል ፡፡  

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3527370
  • Unique Visitors: 199329
  • Published Nodes: 2627
  • Since: 03/23/2016 - 08:03