ናይጀሪያ ላይ በደረሰ የቦንብ አጥፍቶ መጥፋት ጥቃት 50 ሰዎች ሞቱ፡፡

ባህር ዳር: ህዳር 12/2010(አብመድ)በሰሜን ምስራቅ የናይጀሪያ ሙምቢ ግዛት ማንነቱ ባልታወቀ አጥፍቶ ጠፊ በደረሰ ጥቃት 50 ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸው አልፏል፡፡ጥቃቱ የደረሰው በመሰጂድ -ጸሎት ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ ነው እንደፖሊስ ገለጻ፡፡

ባለፉት ጊዚያት አሸባሪው ቦኮሀራም ሀዝብ በሚበዛበት አካባቢ ላለፉት 8 ዓመታት ባደረሰው ጥቃት 20 ሺህ ዎች ህይወታቸው አልፏል፡፡የዛሬውንም ጥቃት ቦኮሀራም ሊፈጽመው እንደሚችል ተገምቷል፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3527343
  • Unique Visitors: 199328
  • Published Nodes: 2627
  • Since: 03/23/2016 - 08:03