ትውልደ ጋናዊው በእንግሊዝ የሳይንስ ሚኒስትር ሆኖ ተሾመ፡፡

ባህርዳር፡ጥር 04 /2010 ዓ/ም(አብመድ)በትውልድ ጋናዊ በዜግነት እንግሊዛዊው የእንግሊዝ ዩኒቨርሲቲዎች እና የሳይንስ ሚኒስትር ሆኖእንዲሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ ሜይ ካቢኔያቸውን እንደገና ባዋቀሩበት ጊዜ መሾሙን አፍሪካ ኒውስ ዘገበ ፡፡

ቀደም ሲል ለምስራቅ ሱሬይ የፓርላማ አባል ሆኖ ያገለገለው የ41 አመቱ ሳም ጋይማህ ቀደም ሲል የማረሚያ ቤቶችና የፍርድ ቤቶች አገልግሎት ሚኒስቴር አደራጅ በመሆን አገልግሏል፡፡

ሳም ጋይማህ አሁን የትራንስፖርት ሚኒስትር የሆነው ጆን ጆንሰን ይዞት የነበረውን ቦታ ነው የተረከበው ፡፡

‹‹ዩኒቨርሲቲዎቻችን በዓለም ውስጥ ከሚገኙ ምርጥ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ተጠቃሽ ከመሆናቸውም በላይ ለእድገታችን ወሳኝ ናቸው ፡፡እኔም የእንግሊዝን ከፍተኛ ትምህርት ለማበረታታት እና ለመደገፍ የምችለውን ሁሉ ለማድረግ እጥራለሁ ››ብሏል አዲሱ ተሿሚ፡፡

በእንግሊዝ ባኪንግሃምሻየር ውስጥ የተወለደው ጋይማህ በእናቱ ጋናዊ ሲሆን በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ፖለቲካል ሳይንስ እና ኢኮኖሚክስ አጥንቷል፡፡

ጋይማህ ወደ ፖለቲካው አለም ከመግባቱ በፊት ለአምስት ዓመታት የተለያዩ የመንግስት ስራዎችን አከናውኗል፡፡

እ.ኤ.አ ከ 2010 ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን መንግስት ውስጥ የፓርላማ ደንብ እና ስነስርአት አስጠባቂ ሆኖ ሲያገለግል እ.ኤ.አ. ከ 2012 እስከ 2013 ባለው ጊዜ ውስጥ የመንግስት ፖሊሲ አስፈጻሚ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የግል ጸሀፊ ሆኖ ሠርቷል፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3884763
  • Unique Visitors: 215543
  • Published Nodes: 2870
  • Since: 03/23/2016 - 08:03