ትራምፕ ስደተኛችን እና ደሃ ሀገራትን አለመሳደባቸውን አስተባበሉ፡፡

ባህርዳር፡ጥር 05 /2010 ዓ/ም(አብመድ)የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከወራት በፊት የተፈጥሮ አደጋ የደረሰባት ሃይቲን፣ኤል ሳልቫዶርን እና የአፍሪካ ሃገራትን አስነዋሪ በሆኑ ዘረኛ ቃላት መሳደባቸውን ዓለም አቀፉ የሰብአዊመብትኮሚሽንአረጋገጠ ፡፡


በቤተመንግስታቸው ከከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸው ጋር በመከሩበት ወቅት ስደተኞችን ‹‹ከቆሸሹ እና ኋላቀር ከሆኑ ሀገራት››የሚመጡ ስደተኞች ጉዳይ ብዙ አይመለከተንም፡፡ይልቁንም ከኖርዌይ እና መሠል ሀገራት የሚመጡ ስደተኞችን ብንከባከብ ነው የሚሻለው ማለታቸውን ሲኤንኤንአስነብቧል፡፡


ይሁን እንጂ እንደተለመደው በትዊተር ገፃቸው እኔ እንዲህ ዓይነት ፀያፍ ቃልም አልተናገርኩም፡፡በእርግጥ የሚሻክር ነገር ተናግሬ ሊሆን ይችላል ፤ ነገር ግን እንደተወራብኝ አይደለም ሲሉ አስተባብለዋል፡፡

በፕሬዝዳንቱ የቃላት ምርጫ እና ደፋር አንደበት የዋሽንግተን ባለስልጣናት እየተሳቀቁ እንደሆነ ቢቢሲ ሲዘግብ ዘረኛ እና አስነዋሪ ቃላት መሠንዘራቸውን ተከትሎ አንድ የተባበሩት መንግስታት ባለስልጣንን ጨምሮ በርካታ ሀገራት ውግዘት እያደረሱባቸው ይገኛሉ፡፡

የነጭ የበላይነትን ይደግፋሉ የሚባሉት ትራምፕ ወደ ለንደን ሊያደርጉ የነበረውን ጉብኝት መሠረዛቸው ሲታወቅ የለንደንከተማኗሪዎችም ጸረ ትራምፕ ተቃውሞ ለማድረግ በዝግጅት ላይ እንደነበሩ የተለያዩ የዜና ምንጮች ዘግበዋል ፡፡

Image: 

Visitors

  • Total Visitors: 3527352
  • Unique Visitors: 199328
  • Published Nodes: 2627
  • Since: 03/23/2016 - 08:03